ምዝገባ

ትኩረት! ሁሉም UNHCR አገልግሎቶች ነፃ ናቸው!

በUNHCR እንዴት መመዝገብ እችላለሁ?

በሊቢያ የጥገኝነት ጠያቂዎች ምዝገባ የሚከናወነው በ UNHCR ነው። በሊቢያ ባለስልጣናት በ UNHCR እንዲመዘገቡ የተፈቀደላቸው የተወሰኑ ሀገር ዜግነት ያላቸው ሰዎችን ብቻ ነው።

የመመዝገቢያ የስልክ መስመራችንን በ 📞 0911633466 መደወል ትችላላችሁ፣የምዝገባ ሰራተኛ የምዝገባ አሰራርን በተመለከተ ምክር ይሰጥዎታል። ብቁ ከሆኑ፣ ከ UNHCR ሰራተኞች ጋር በትራብሎስ ወይም ሌላ ምዝገባ በሚካሄድበት ቦታ ለመገናኘት የቀጠሮ ቀን ይሰጥዎታል። በምዝገባ ቃለ መጠይቅዎ ወቅት UNHCR ስለእርስዎ ስም፣ የትውልድ ቀን፣ የትውልድ ቦታ እና የትውልድ ሀገርዎን የለቀቁበትን ምክንያት ጨምሮ መረጃ ይሰበስባል።

ወደ የምዝገባ ቃለ መጠይቁ ምን ላምጣ?

በምዝገባ ቀን ሁሉም የቤተሰብዎ አባላት (የትዳር አጋር፣ ልጆች ወይም ሌሎች የቅርብ የቤተሰብ አባላት ጥገኞች) ከእርስዎ ጋር መሆን አለባቸው።

የሚከተሉትን ጨምሮ ያልዎትን ሁሉንም ዋና ሰነዶች ይዘው መምጣት አለብዎት።

  • ፓስፖርት
  • የብሔራዊ መታወቂያ ካርድ
  • የልደት ምስክር ወረቀት
  • የሥራ ፈቃድ
  • ከጋብቻዎ ሁኔታ ጋር በተያያዘ የምስክር ወረቀቶች
  • የትምህርት መዝገቦች
  • ከሌላ ሀገር የተገኘ የዩኤንኤችአር ወይም የመንግስት የስደተኛ ወይም የጥገኝነት ጠያቂነት ሰርተፍኬት
  • ስለ ማንነትዎ የሚገልጽ ማንኛውም ሌላ ኦፊሴላዊ ሰነዶች

እንዲሁም ከትውልድ ሀገርዎ ከወጡበት ምክንያት ጋር የተዛመዱ ከመሰለዎት ሌሎች ሰነዶችን ይዘው መምጣት ይችላሉ።

እባክዎ ምንም ሰነድ ባይኖርዎትም በ UNHCR መመዝገብ እንደሚችሉ ልብ ይበሉ።

የUNHCR ሰነዴን እንዴት ማደስ እችላለሁ?

የመመዝገቢያ የስልክ መስመራችንን በ 📞 0911633466 ይደውሉ።በUNHCR ትራብሎስ ወይም በሌላ ቦታ ጋር ቀጠሮ ይሰጥዎታል።

የአድራሻዬ ዝርዝሮች እንዴት ማዘመን እችላለሁ?

📞 0911633466 መመዝገቢያ ስልክ መስመራችን  የ UNHCR የጉዳይ ቁጥር ፣አዲሱ አድራሻዎ እና ስልክ ቁጥርዎን አካተው በመሴጅ መልእክት መላክ ይችላሉ። መልእክቱን በኤስኤምኤስ፣ በዋትስአፕ ወይም በቫይበር መላክ ይችላሉ።

የአድራሻ ዝርዝሮችዎ በሰባት የስራ ቀናት ውስጥ በእኛ ፋይል ጎታ ውስጥ ይስተካከላሉ። መረጃዎ መዘመኑን የሚያረጋግጥ መልእክት ይደርስዎታል።

የቤተሰብ አባላትን ወደ ጉዳዬ እንዴት ማካተት እችላለሁ?

የመመዝገቢያ የስልክ መስመራችንን በ 📞 0911633466 ይደውሉ። ወደ UNHCR ትራብሎስ ጽህፈት ቤት ወይም UNHCR የምዝገባ ስራዎችን በሚያከናውንበት ሌላ ቦታ  ቀጠሮ ይሰጥዎታል።

የእኔ ፋይል ተዘግቷል። እንደገና እንዲከፈት እንዴት ልጠይቅ እችላለሁ?

ፋይልዎ የተዘጋ ወይም የማይንቀሳቀስ ከሆነ፣የእኛን የምዝገባ የስልክ መስመር በ 📞 0911633466 በመደወል የመመዝገቢያ ቀጠሮ መያዝ አለቦት። በቀጠሮው ቀን UNHCR ፋይልዎን እንደገና ለመክፈት ወይም ለማንቀሳቀስ አስፈላጊውን መረጃ ለመሰብሰብ ፎርም እንዲሞሉ ይጠይቅዎታል።

እባክዎ ፓስፖርትዎን እና ሁሉንም የግል መታወቂያ ሰነዶችን ይዘው ይምጡ።

በአሁኑ ጊዜ በእስር ቤት ታስሬያለሁ እና በUNHCR መመዝገብ እፈልጋለሁ። ምን ላድርግ?

UNHCR በአስር ቤት ማእከላት የምዝገባ ስራዎችን አያከናውንም። ሆኖም UNHCR እንዲፈቱ ይከራከራል እና ከተለቀቁ በኋላ የምዝገባ ቀጠሮ ይሰጥዎታል።


<< ወደ ሊቢያ መነሻ ገጽ ተመለስ >> በእገዛ ገጻችን ላይ ሌላ አገር ይምረጡ