ህክምና እና የአእምሮ ጤንነት

ሌሎች ሰብአዊ መብቶችን ለመጠቀም ጤና የማግኘት መብት አስፈላጊ ነው። ይህ መብት መሰረታዊና አካታች መብት ሲሆን:  ወቅታዊ እና ተገቢ የጤና እንክብካቤ እና ንፁህ የመጠጥ ውሃ: ንፁህና በቂ የሆነ እንዲሁም ደህንነቱ የተጠበቀ ምግብና የመኖሪያ ቤት አቅርቦት፣ጤናማ የሥራ እና የአካባቢ ሁኔታዎች፣  ከጤና ጋር የተያያዘ ትምህርት እና መረጃ ማግኘት መብቶችን ያጠቃልላል::  UNHCR ከሊቢያ የጤና ባለሙያዎች ጋር ይሰራል እንዲሁም አስፈላጊ የጤና አገልግሎቶችን በበቂ ሁኔታ ለማቅረብ፣ የአካባቢ ጤና አገልግሎቶችን ለማሻሻል እና ስደተኞችን እና ጥገኝነት ጠያቂዎችን በሀገራዊ የጤና ስርአት ውስጥ ለማካተት ከሌሎች የጤና አጋሮች ጋር በጤና የስራ ቡድን በኩል ይሰራል።

አጋራችን ዓለም አቀፍ የነፍስ አድን ኮሚቴ (IRC) ለስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች በትራብሎስ በሚገኘው የማህበረሰብ እርዳታ ማእከል (CDC) እንዲሁም የመጀመሪያ ደረጃ የጤና እንክብካቤ ማእከላት የጤና አገልግሎቶችን ጨምሮ በርካታ አገልግሎቶችን ይሰጣል፡-

አልምጋሪፍ የሕዝብ ጤና ጣቢያ (ረቡዕ ፣ ሐሙስ)

ዛውየትአል-ዲህማኒ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና እንክብካቤ ማዕከል (እሑድ ፣ ሰኞ ፣ ማክሰኞ)

አጋራችን  CESVI የስነ-ልቦና እና የአእምሮ ጤና አገልግሎቶች ለሚያስፈልጉአቸው  ለስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች  ይሰጣል። አጋራችን  IRC ደግሞ የአእምሮ ጤና ምክክርን ጨምሮ የአእምሮ ጤና እና የስነ-ልቦና-ማህበራዊ ድጋፍ አገልግሎቶችን ይሰጣል።

የሕክምና እርዳታ እፈልጋለሁ፤ ምን ማድረግ አለብኝ?

የጤና አገልግሎት በUNHCR አጋር ዓለም አቀፍ የነፍስ አድን ኮሚቴ (IRC) አማካኝነት ይሰጣል። አገልግልቱ የሚሰጠው በቀጠሮ እና በየቀኑ  ለተወሰኑ  ግለሰቦች ብቻ ስለሆነ: አጣዳፊ ላልሆኑ ጉዳዮች በሚከተለው ስልክ በመደወል ቀጠሮ ማስያዝ ያስፈልግዎታል።

ጠቅላላ ምክር፡ 📞0910347365

የስነ ተዋልዶ ጤና እና የቅድመ ወሊድ ምክር: 📞 0910354818

የአገልግሎት ሰአታት፡- ከእሁድ እስከ ሀሙስ ከ09፡00 እስከ 16፡30

አስቸኳይ የህክምና ጉዳይ ስላለብኝ አፋጣኝ የህክምና እርዳታ እፈልጋለሁ። ምን ማድረግ አለብኝ?

ለሕይወት አስጊ የሆነ የሕክምና ድንገተኛ አደጋ ሲያጋጥም፣ እባክዎን ወደ 📞 0910354839 (24/7) በማንኛውም ቀን እና ሰአት) ይደውሉ፤ IRC (ዓለም አቀፍ የነፍስ አድን ኮሚቴ) የድንገተኛ ሕክምና ቡድን ይረዳችኋል።

የስነ ልቦና ድጋፍ ማግኘት እፈልጋለሁ። እንዴት ልጠይቅ እችላለሁ?

ከቀኑ 9፡00 እስከ 17፡00 ከእሁድ እስከ ሐሙስ በ 📞 0910027717 ወይም 📞 0922767166 በመደወል ከ CESVI ጋር ቀጠሮ ማስያዝ ይችላሉ።


<< ወደ ሊቢያ መነሻ ገጽ ተመለስ >> በእገዛ ገጻችን ላይ ሌላ አገር ይምረጡ