የስነ ምግባር ጉድለት ሪፖርት ማድረግ(ማሳወቅ)

ትኩረት! ሁሉም የዩኤንኤችአር አገልግሎቶች ነፃ ናቸው!

የእርስዎ ሪፖርት በጥንቃቄ እና በጥብቅ ሚስጥር ይያዛል።

ስነ ምግባር ጉድለት ምንድን ነው?

የስነምግባር ጉድለት አንድ ሰራተኛ “በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቻርተር፣ የሰራተኞች ህግ እና የሰራተኛ ደንብ ወይም ሌሎች አስተዳደራዊ ጉዳዮችን ደምብ ሳያከብር ወይም ከአለም አቀፍ ሲቪል ሰርቫንቱ የሚጠበቀውን የስነምግባር እና የሚጠበቅበትንን ግዴታዎች ለመወጣት አለመቻል ነው።

የስነ ምግባር ጉድለት ዓይነቶች ምንድናቸው ናቸው?

  •  ጾታዊ ብዝበዛ እና ባለ ጉዳይ ላይ የሚደርስ ጥቃት።
  • ማጭበርበር (ለምሳሌ፡ ጥቅም ለማግኘት ሰነድ ማጭበርበር)።
  • ሙስና (ለምሳሌ፡ ከስደተኞች ወይም ከሌሎች ገንዘብ መውሰድ)።
  • ከምዝገባ እና ከሶተኛ ሀገር መቋቋም ሂደት ጋር የተያያዘ ማጭበርበር።
  • ስርቆት እና ምዝበራ (ለምሳሌ፡ ንብረት ወይም ገንዘብ መስረቅ)።
  • በሥራ ቦታ የሚደርስ ትንኮሳ (ለምሳሌ፡ የሰራተኛ አባላትን ኢፍትሃዊ በሆነ መንገድ ማስተናገድ)።
  • ወሲባዊ ትንኮሳ (ለምሳሌ፡ ያልተፈለገ ወሲባዊ ትንኮሳ)።
  • ስልጣንን አላግባብ መጠቀም (ለምሳሌ፡ ማዳላት ወይም በሰራተኞች ላይ ልዩነት ማሳየት)።
  • በሌሎች ላይ ጥቃት ወይም ዛቻ።
  • የ UNHCR ንብረቶችን አላግባብ መጠቀም።
  • ሚስጥራዊነትን መጣስ።
  • UNHCRን የሚያሳጣ ተግባር ወይም ባህሪ።
  • የአካባቢ ህጎችን አለማክበር።
  • የፍላጎት ግጭት.
  • መብቶችን እና ከለላዎችን አላግባብ መጠቀም።
  • ከፍተኛ ቸልተኝነት።
  • ያልተፈቀዱ የውጭ እንቅስቃሴዎች ወይም የሥራ ቅጥር

በ UNHCR ለመመዝገብ ገንዘብ እየተጠየቅኩ ነው? ምን ላድርግ?

ለስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች የሚቀርቡት ሁሉም የእርዳታ እና የከለላ አገልግሎቶች ከክፍያ ነጻ ናቸው። እባክዎን ለማንኛውም UNHCR ወይም አጋር ለሚሰጡ አገልግሎቶች ማንኛውንም ገንዘብ መክፈል፣ ውለታ መዋል፣ አግዝሀለሁ አድርግልኝ በማለት በአካልም ሆነ ቁሳቁስ (ገንዘብ ፣ ወይም ማንኛውንም ዕቃ ወይም አገልግሎቶችን ጨምሮ) ማድረግ የለብዎትም።

ይህንን ጥሰት በሚስጥር ለ UNHCR ማሳወቅ ይችላሉ። ማጭበርበርን፣ ሙስናን፣ ጾታዊ ጥቃትን ወይም ብዝበዛን ወይም ሌሎች ጥፋቶችን ሪፖርት ለማድረግ የ UNHCR ዋና ኢንስፔክተር ቢሮን ያነጋግሩ፡-

የ UNHCR ሊቢያ ቅሬታ ሣጥኖች በሴራጅ ቢሮ ውስጥ ይገኛሉ። የቅሬታ ሂደቱ የስነምግባር ጥፋቶች ሰለባ እንደሆኑ የሚያምኑ ጥገኝነት ጠያቂዎች ወይም ስደተኞች በUNHCR ሰራተኞች፣ አስተርጓሚዎች ወይም ጠባቂዎች ከባድ ስለተሳሳተ ባህሪ መረጃ ለ UNHCR ከፍተኛ አመራሮች እንዲያቀርቡ ያስችላቸዋል። የ UNHCR የአቤቱታ ስርዓት በአንድ የ UNHCR ሰራተኛ፣ አስተርጓሚ ወይም የጥበቃ ሰራተኛ የተፈጸመ ከባድ የስነምግባር ጥሰት ወይም ኢፍትሃዊ አሰራር ጉዳዮችን ይመለከታል።

ቅሬታ ለመጀመር እባክዎን ቅሬታዎን በታሸገው የቅሬታ ሳጥን ውስጥ ያስገቡ። በሊቢያ የቅሬታ ሳጥን ማግኘት የሚችለው በጣም ከፍተኛ የ UNHCR ሰራተኛ ብቻ ነው እንዲሁም ቅሬታዎ በሚስጥራዊ መንገድ ያስተናግዳል።

እባክዎ ያስታውሱ UNHCR እና አጋሮቹ በፖሊስያቸው ማጭበርበር፣ ሙስና፣ ወሲባዊ ብዝበዛ፣ ትንኮሳ እና እንግልት/ጥቃት በተመለከተ በከፍተኛ ደረጃ ከማይታገሳቸው ጉዳዮች ናቸው።

ከ UNHCR ወደ ማቆያ ሀገር ለመብረር የሚደረግ ቃለ መጠይቅ ለማድረግ ገንዘብ እየተጠየቅኩ ነው? ምን ላድርግ?

ለስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች የሚቀርቡት ሁሉም የእርዳታ እና የከለላ አገልግሎቶች ከክፍያ ነጻ ናቸው። እባክዎን ከ UNHCR ወይም ከአጋሮቻችን እርዳታ ለማግኘት ምንም አይነት ገንዘብ መክፈል ወይም ምንም አይነት ውለታ መዋል እንደሌለብዎት ይወቁ።ጥሰት ካጋጠመ በሚስጥር ለ UNHCR ማሳወቅ ይችላሉ። ማጭበርበርን፣ ሙስናን፣ ጾታዊ ጥቃትን ወይም ብዝበዛን ወይም ሌሎች ጥፋቶችን ሪፖርት ለማድረግ የ UNHCR ዋና ኢንስፔክተር ቢሮን ያነጋግሩ፡-

የ UNHCR ሊቢያ ቅሬታ ሣጥኖች በሴራጅ ቢሮ ውስጥ ይገኛሉ። የቅሬታ ሂደቱ ጥገኝነት ጠያቂዎች ወይም ስደተኞች በUNHCR ሰራተኞች፣ አስተርጓሚዎች ወይም ጠባቂዎች ከባድ የስነምግባር ጥፋቶች ሰለባ እንደሆኑ የሚያምኑ ስለተሳሳተ ባህሪ መረጃ ለ UNHCR ከፍተኛ አመራሮች እንዲያቀርቡ ያስችላቸዋል። የ UNHCR የአቤቱታ ስርዓት የአንድ የ UNHCR ሰራተኛ፣ አስተርጓሚ ወይም የጥበቃ ሰራተኛ ከባድ የስነምግባር ጥሰት ወይም ኢፍትሃዊ አሰራር ጉዳዮችን ይመለከታል።

ቅሬታ ለመጀመር እባክዎን ቅሬታዎን በታሸገው የቅሬታ ሳጥን ውስጥ ያስገቡ። በሊቢያ የቅሬታ ሳጥን ማግኘት የሚችለው በጣም ከፍተኛ የ UNHCR ሰራተኛ ብቻ ነው እንዲሁም ቅሬታዎ በሚስጥራዊ መንገድ ያስተናግዳል።

እባክዎ ያስታውሱ UNHCR እና አጋሮቹ በፖሊስያቸው ማጭበርበር፣ ሙስና፣ ወሲባዊ ብዝበዛ፣ ትንኮሳ እና እንግልት/ጥቃት በተመለከተ በከፍተኛ ደረጃ ከማይታገሳቸው ጉዳዮች ናቸው።

ማጭበርበር ምንድን ነው? በስደተኞች፣ ጥገኝነት ጠያቂዎች ወይም ሌሎች ግለሰቦች የጠረጠርኩትን ማጭበርበር እና ሙስና እንዴት ሪፖርት አደርጋለሁ?

ማንኛውም ድርጊት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለራስ ወይም ለሌላ ሰው ጥቅም ለማስገኘት በማወቅ ወይም ሆን ተብሎ የተሳሳተ መረጃ ማቅረብ፣መደበቅ ወይም ለማሳሳት መሞከር ነው።

የማጭበርበር ድርጊቶች ምሳሌዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ:

  • አንድ ሰው የግል ሁኔታ የእርዳታ ወይም አገልግሎት ጥቅም ለማግኘት ሲባል የተሳሳተ መረጃ መስጠት፣
  • የተጭበረበሩ ሰነዶችን ወይም እውነተኛ ሰነዶችን በውሸት መንገድ መጠቀም፣
  • ለግል ጥቅም ገንዘብ መጠየቅ ወይም የእርዳታ ወይም አገልግሎት ጥቅም ለማግኘት ገንዘብ መክፈል (ለምሳሌ፡ ምዝገባ፣ ወደ ሶስተኛ ሀገር መልሶ መቋቋም)፣
  • UNHCRን፣ ሌሎች አካላትን ወይም አጋር ድርጅቶቻችን እወክላለሁ በማለት በውሸት መቅረብ።

እባክዎን በስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች የተፈፀሙ ማጭበርበር እና ሙስና ስጋቶች ወይም ጥርጣሬዎች ለ 📧 [email protected] ያሳውቁ። ሁሉም ሪፖርቶች በጥብቅ ሚስጥራዊነት ይያዛሉ.

የ UNHCR ሰራተኞች፣ ተርጓሚዎች፣ የጥበቃ ሰራተኞች እና/ወይም አጋሮች በሚያካትቱ የስነምግባር ጉድለቶች የሚመለከት እንዴት ቅሬታዋቼን ማቅረብ እችላለሁ?

ይህንን ጥሰት በሚስጥር ለ UNHCR ማሳወቅ ይችላሉ። ማጭበርበርን፣ ሙስናን፣ ጾታዊ ጥቃትን ወይም ብዝበዛን ወይም ሌሎች ጥፋቶችን ሪፖርት ለማድረግ የ UNHCR ዋና ኢንስፔክተር ቢሮን ያነጋግሩ፡-

ቅሬታ ለመጀመር እባክዎን ቅሬታዎን በታሸገው የቅሬታ ሳጥን ውስጥ ያስገቡ። በሊቢያ የቅሬታ ሳጥን ማግኘት የሚችለው በጣም ከፍተኛ የ UNHCR ሰራተኛ ብቻ ነው እንዲሁም ቅሬታዎ በሚስጥራዊ መንገድ ያስተናግዳል።

ለስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች የሚቀርቡት ሁሉም የእርዳታ እና የከለላ አገልግሎቶች ከክፍያ ነጻ ናቸው። እባክዎን ከ UNHCR ወይም ከአጋሮቻችን እርዳታ ለማግኘት ምንም አይነት ገንዘብ መክፈል ወይም ምንም አይነት ውለታ መዋል እንደሌለብዎት ይወቁ።

ወሲባዊ ብዝበዛ እና በደል ምንድን ነው?

አቋማችን ግልጽ እና በተለያዩ ጊዜያት በከፍተኛ ኮሚሽነራችን ተደጋግሞ ተነግሯል፡-

  • ፆታዊ ትንኮሳ የማይገባ እና ከ UNHCR ስራዎች መጥፋት ያለበት ነው።
  • ወሲባዊ ብዝበዛ እና በደል ባለ ጉዳዮቻችንን ይጎዳል።
  • ወሲባዊ ብዝበዛ ማለት የአንድን ሰው የተጋላጭነት ሁኔታ አላግባብ መጠቀም ማለት ነው (ለምሳሌ፡ ለምግብ ፣ ለትምህርት ቤት መጽሐፍት ፣ ለትራንስፖርት ወይም ለሌላ አገልግሎቶች እርስዎ ላይ ጥገኛ የሆነን) ፣ ልዩ ኃይል ወይም እምነት በመጠቀም ወሲባዊ ጥቅሞችን ለማግኘት ሆኖ ነገር ግን ገንዘብን ወይም ሌሎች ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ወይም ፖለቲካዊ ጥቅሞችን ማቅረብ እንዲሁም የሰዎች ዝውውር እና ዝሙትን ያጠቃልላል።
  • • ጾታዊ ጥቃት ማለት በድርጊት ወይም ወሲባዊ ነክ የሆነ ዛቻ  በጉልበት፣ እኩል ባልሆነ ወይም አስገዳጅ ሁኔታ ሲከናወን ማለት ነው። ወሲባዊ ባርነትን፣ የብልግና ምልክቶችን፣ የሕጻናት ጥቃትን እና ወሲባዊ ጥቃትን ያጠቃልላል።

ወሲባዊ ብዝበዛን እና ጥቃት እንዴት ሪፖርት አደርጋለሁ?

በUNHCR፣ UN ወይም NGO ባልደረባ ሊደርስ ስለሚችለው የወሲብ ብዝበዛ እና በደል ጉዳይ የምታውቁ፣ ወይም ስጋት ወይም ጥርጣሬ ካለህ፣ እባኮትን በቀጥታ በUNHCR ዋና መሥሪያ ቤት ለኢንስፔክተር ጄኔራል ጽሕፈት ቤት (IGO) ያሳውቁ፡

ለበለጠ መረጃ፡ UNHCR – ወሲባዊ ብዝበዛ እና ጥቃት ሪፖርት ማድረግ (SEA) መጎብኘት ትችላለህ።

ስነ ምግባር ጉድለትን ሪፖርት ሳደርግ ምን ማካተት አለብኝ?

ለ UNHCR እውነተኛ እና የተሟላ መረጃ መስጠት አስፈላጊ ነው። እባክዎ ከታች ያለውን መረጃ በተቻለዎት መጠን ያካትቱ፡

  • ምን አይነት ጥፋት ነው የሚያሳውቁት? የሚያውቁትን ብዙ ዝርዝሮችን ጨምሮ ምን እንደተፈጠረ ይግለጹ።
  • የተጠረጠረውን ጥፋት የፈጸመው ማን ነው? ሌላ ሰው ተሳታፊ እንደነበረ ያውቃሉ? ከተቻለ ሙሉ ስም፣ ምን እንደሚሰራ እና የሚሰራበት ድርጅት ያቅርቡ።
  • ክስተቱ(ቶቹ) መቼ እና የት ተከሰተ? የሚያስታውሱ ከሆነ ቀኑን እና ሰዓቱን ይግለጹ።
  • ግለሰቡ የተጠረጠረውን ጥፋት እንዴት ፈጸመ?
  • የተፈጸመው ነገር ትክክል አይደለም ብለው እንዴት አመኑ?

እባክዎን ክስዎን የሚያረጋግጡ ደጋፊ ማስረጃዎች ካሉዎት ማጋራት እንደሚችሉ ማሳወቅ እንወዳለን።


<< ወደ ሊቢያ መነሻ ገጽ ተመለስ >> በእገዛ ገጻችን ላይ ሌላ አገር ይምረጡ