ስለ UNHCR ሊቢያ

UNHCR በሊቢያ ያለው ሚና ምንድን ነው?

የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኤጀንሲ(UNHCR)  በ1951 የስደተኞች ስምምነት መሰረት አለም አቀፍ ከለላን የመስጠት እና ለስደተኞች ችግር  መፍትሄዎችን የማፈላለግ ስልጣን የተሰጠው ድርጅት ነው። UNHCR የማንም ሰው ጥገኝነት የመጠየቅ መብትን ለማስከበር እና በሌላ ግዛት ውስጥ ደህንነቱ እንዲጠበቅና የከለላ መብት እንዲያገኝ ይሰራል፤ እንዲሁም ወደ ሀገር ቤት የመመለስ፣ ጥገኝነት ከሰጠው ማህበረሰብ ጋር የመዋሃድ ወይም ወደ ሶስተኛ ሀገር የመሄድ አማራጭ ዕድሎችን የማሳለጥ ስራ ይሰራል::  በስደት ወቅት፣ UNHCR ህጋዊ እና አካላዊ ከለላ በመስጠት የፆታዊ ጥቃትን ጨምሮ የጥቃት ስጋቶችን ለመቀነስ ይሰራል። በተጨማሪም የስደተኞች  መሰረታዊ ፍላጎቶቹ: ማለትም መጠለያ፣ ምግብ፣ ውሃ እና የህክምና አገልግሎት እንዲሟሉ ይሰራል።

ሊቢያ፣ UNHCR የሊቢያ ባለስልጣናት ለተፈናቀሉ እና በግጭት ለተጎዱ ሊቢያውያን ድጋፍ እንዲያደርጉና  የኑሮ ሁኔታቸውን እንዲያሻሽሉ ድጋፍ ያደርጋል:: እንዲሁም በተለይ ለ ችግር ተጋላጭ የሆኑትን ጥገኝነት ጠያቂዎችን እና ስደተኞችን ለመርዳት ከአጋሮቹ ጋር በመሆን ይሰራል።

ማንን ነው የምንረዳው?

  • ጥገኝነት ጠያቂዎች: ጥገኝነት ጠያቂ የአለም አቀፍ ከለላን የሚፈልግ እና አሁንም ማመልከቻው በሂደት ላይ ያለ ግለሰብ ነው። በሊቢያ፣ በ UNHCR የተዘጋጀ  የጥገኝነት ጠያቂ ሰርተፍኬት ይሰጣቸዋል።
  • ስደተኞች: ስደተኛ ማለት በዘር፣ በሀይማኖት፣ በብሄረሰብ፣ በአንድ የተወሰነ የማህበረሰብ ቡድን አባልነት ወይም በፖለቲካዊ አመለካከት ምክንያት ጉዳት ይደርስብኛል በሚል ፍራቻ ወደ ትውልድ አገሩ መመለስ የማይችል ወይም ፈቃደኛ ያልሆነ ሰው ነው። በሊቢያ በ UNHCR የተዘጋጀ  የስደተኛ ሰርተፍኬት ይሰጣቸዋል።
  • በአገር ውስጥ የተፈናቀሉ ሰዎች: በአገር ውስጥ የተፈናቀሉ ሰዎች (IDP) ቤት ንብረታቸውን ጥለው የተሰደዱ፣ ነገር ግን እንደ ስደተኞች ሳይሆን በአገራቸው ድንበሮች ውስጥ የቆዩ ናቸው። በሊቢያ፣ በUNHCR እና በአጋሮቹ ከሚሰጡት አንዳንድ አገልግሎቶች ተጠቃሚ ሊሆኑ ይችላሉ።

በሊቢያ UNHCRን እንዴት ማግኘት ይቻላል?

በሊቢያ UNHCR ቢሮ በትራብሎስ ይገኛል፡-

ሰራጅ ምዝገባ ማዕከል

ሰሀል አልጃፋራ መንገድ፣ ከአልማሽቴል ማዞሪያ ቀጥሎ፣ ሰራጅ አካባቢ፣ ትራብሎስ

ወደ UNHCR ቢሮ በአካል ከመሄድዎ በፊት፣ እባክዎ ይደውሉ እና ቀጠሮ እንዲሰጥዎ ይጠይቁ።

UNHCRን በስልክ ያነጋግሩ፡-

  • UNHCR የመመዝገቢያ ስልክ 📞 0911633466 (ከእሁድ እስከ ሐሙስ 08፡30-16፡30)

የ UNHCR ሊቢያን የፌስቡክ ገጽ ለመጎብኘት እዚህ ጠቅ ያድርጉ።


ሁሉም የUNHCR አገልግሎቶች ነፃ ናቸው! ጠቃሚ መረጃ፡- << ወደ ሊቢያ መነሻ ገጽ ተመለስ >> በእገዛ ገጻችን ላይ ሌላ አገር ይምረጡ