ጥበቃ

UNHCR እና በሊቢያ ውስጥ ያሉ አጋሮች እንደ ጥሬ ገንዘብ፣ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ እቃዎች (NFI)፣ የምክር አገልግሎት፣ የስነ-ልቦና እና የማህበረሰብ ድጋፍን ጨምሮ ብቁ ለሆኑ ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች የተለያዩ አገልግሎቶችን ይሰጣሉ። የእርስዎን ፍላጎቶች እና ለተለያዩ አገልግሎቶች ብቁ መሆንዎን ለመወሰን በመጀመሪያ በUNHCR ወይም በአጋር ድርጅቶች የጥበቃ ፍላጎት ግምገማ ሊደረግልዎ ይገባል።

በከለላ ፍላጎቶች ግምገማ በሊቢያ ያለዎትን ሁኔታ በማጥናት ላሉት አገልግሎቶች እና እርዳታ ብቁ መሆንዎን ይወስናል። የብቃት መስፈርት ካላሟሉ ወይም የሚፈልጉት ልዩ ድጋፍ በUNHCR እና/ወይም በአጋሮች ካልተሰጠ ቃለ መጠይቅ ስላደረጉ ብቻ እርዳታ እና አገልግሎት እንደሚያገኙ ዋስትና አይደለም።

ከ UNHCR ጋር የከለላ ቃለ መጠይቅ እንዲደረግልኝ እፈልጋለሁ። እንዴት ልጠይቅ እችላለሁ?

በUNHCR እና CESVI የሚደረጉ የከለላ ፍላጎቶች ጥናት በከተሞች ውስጥ በጣም ተጋላጭ ለሆኑ ግለሰቦች ከከለላ እርዳታ እና ድጋፍ ጋር የተቆራኙ ናቸው። በቃለ መጠይቁ ባህሪ ምክንያት የከለላ ፍላጎቶች ጥናት የሚደረጉት የተወሰኑ የከለላ አደጋ እና ስጋቶች ሲኖሩ ብቻ ነው። ከዚህ ቀደም ያላደረጉ ከሆነ እና ስለ ከለላ ጉዳዮችዎ ሪፖርት ለማድረግ እና ግምት ውስጥ መግባት ይችሉ እንደሆነ ለማየት ወደ UNHCR፣ CESVI ወይም Tawasul የስልክ መስመር መደወል ይችላሉ። ከዚህ ቀደም አድርገው ከሆነ፣ እና በእርስዎ ሁኔታ ላይ ምንም አይነት ትልቅ ለውጥ ከሌለ እንደገና ቃለ መጠይቅ አይደረግልዎትም።

የከለላ ቃለመጠይቆች ወደ ዘላቂ መፍትሄዎች መንገድ አይደሉም።

UNHCR ከለላ ስልክ መስመር፡ 📞 0917127644

Tawasul – የጋራ ግብረመልስ ዘዴ መስመር፡ 📞 1404

CESVI የስልክ መስመሮች (ከእሁድ እስከ ሐሙስ፣ 09.00 እስከ 17.00)፡

  1. 📞 092 2767166
  2. 📞 091 0027716

የፆታዊ ጥቃት ሰለባ ነኝ። አገልግሎቶች እንዴት ማግኘት እችላለሁ?

የጾታዊ ጥቃት ሰለባ ከሆኑ አስቸኳይ የጤና አገልግሎት ማግኘት ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው ስለዚህ ጤናዎን ለመጠበቅ ክስተቱ በተፈጠረ በ72 ሰአታት ውስጥ ወዲያውኑ የሚገኝ የህክምና አገልግሎት መሄድ አለብዎት።

እባክዎን በ 📞 0910354839 (24 ሰዓት 7 ቀን) ይደውሉ፡ IRC(አለምአቀፍ አድን ኮሚቴ)  የድንገተኛ ህክምና ቡድን ይረዳዎታል።

ጾታ-ተኮር ጥቃት ሰለባ የሆኑ እና ወሲባዊ ጥቃት ወይም ትንኮሳ ያጋጠማቸው የሚያግዙ የሚመለከታቸው ድርጅቶች አሉ። በልዩ ሁኔታ በሙያው የሰለጠነ ጉዳዩ ከሚመለከተው ድርጅት የሆነ ሰራተኛ አስፈላጊ የሆኑ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ ድጋፍ ሊደረግልዎ ይችላል። በተጨማሪ ከፈለጉ ደሞ የአእምሮ ጤና እና የስነ-ልቦና አገልግሎቶች፣ከማህበረሰብ ተንከባካቢ ጋር መኖርያ፣የህግ መረጃ እና ምክር፣ የገንዘብ እርዳታ፣ እና ምግብ ያልሆኑ እቃዎች እርዳታን ያጠቃልላል። ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች ሰለባዎች ጋር የሚሰሩ ማናቸውም ድርጅቶች ዋስትና እና ለደህንነትዎ ቅድሚያ ሊሰጡ ይገባል፣ በሚያጋሩት መረጃ ውስጥ ምስጢራዊነትን ማረጋገጥ፣ የኋላ ታሪክዎ ምንም ይሁን ምን እኩል እና ፍትሃዊ አያያዝን ማረጋገጥ እና በየትኛው አገልግሎት ላይ የእርስዎን አስተያየት እና ምርጫዎች ማክበር አለባቸው።

ድጋፍ ለማግኘት በዚህ መደወል ይችላሉ፡-

CESVI የስልክ መስመሮች (ከእሁድ እስከ ሐሙስ፣ 09.00 እስከ 17.00)፡

  1. 📞 092 2767166
  2. 📞 091 0027716

UNHCR ከለላ የስልክ መስመር፡ 📞 0917127644


<< ወደ ሊቢያ መነሻ ገጽ ተመለስ >> በእገዛ ገጻችን ላይ ሌላ አገር ይምረጡ