ምግብ ነክ ያልሆኑ እቃዎች (NFIs) እና መጠለያ

እንደ መሪ ምግብ ነክ ያልሆኑ ነገሮች (NFI) እገዛ ኤጀንሲ፣ ምግብ ነክ ያልሆኑ ነገሮች  ስርጭት ለ UNHCR ሊቢያ ኦፕሬሽን በጣም ወሳኝ ከሆኑ ተግባራት ውስጥ አንዱ ነው። በአጋሮቻችን በአለም አቀፍ የነፍስ አድን ኮሚቴ (IRC) እና በሊቢያ የሰብአዊ እርዳታ ኤጀንሲ (LibAid)፣ በችግር ውስጥ ያሉትን በጣም ተጋላጭ የሆኑትን ከባህር ማእበል የተረፉ:  በከተማ እና እስር ቤት ማእከላት የሚገኙ ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎችን እንዲሁም እንደ የህይወት አድን ተግባራችን በባህር የሚያዙትንም እናግዛለን።

ዋና የእርዳታ እቃዎችን (የምግብ ነክ ያልሆኑ እቃዎችን) እንዴት መጠየቅ እችላለሁ?

የ UNHCR ከለላ መስመር 📞 0917127644 ወይም CESVI የስልክ መስመር 📞 0910027717 እና 📞 0922767166 በመደወል ጥያቄዎን ማስረዳት ይችላሉ።

ብቁ ከሆኑ እና እቃዎቹ ካሉ፣ እቃዎቹን እንዴት መቀበል እንደሚችሉ ለማሳወቅ በUNHCR አጋር IRC መረጃ ይሰጥዎታል::

UNHCR ቤት እንዳገኝ ሊረዳኝ ይችላል?

UNHCR መጠለያ ባይሰጥም፣ በጣም ተጋላጭ ለሆኑ ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች የቁሳቁስ ድጋፍ ያደርጋል::

ድጋፍ የሚያፈልግዎ ከሆነ እባክዎን ሁኔታዎን ከታች ካሉት የጥሪ ማእከሎች ባንዱ ደውለው  ያስረዱ

  • UNHCR ከለላ(Protection) መስመር 📞 0917127644
  • CESVI  ስልክ 0910027717 እና 📞 0922767166
  • Tawasul – የጋራ የግብረመልስ ዘዴ 📞 1404

ለድጋፍ ብቁ ከሆኑ ለተጨማሪ ግምገማ ወይም እርዳታ እናገኞታለን።


<< ወደ ሊቢያ መነሻ ገጽ ተመለስ >> በእገዛ ገጻችን ላይ ሌላ አገር ይምረጡ