ሶስተኛ ወይም ማሸጋገርያ ሀገር መሄድ

ትኩረት! ሁሉም የዩኤንኤችአር አገልግሎቶች ነፃ ናቸው!

በረራ ወደ መቆያ ሀገር ምንድን ነው? የመሄጃ መስፈርቶች ምንድን ናቸው?

ወደ መቆያ ሀገር የሚደረጉ በረራዎች በ UNHCR የሚዘጋጁ ሆነው በሊቢያ እና በተቀባይ ሀገራት መንግስታት ድጋፍ ሲሆን ይህም አንዳንድ በጣም ተጋላጭ የሆኑ ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ከሊቢያ  ጊዚያዊ ዋስትና ወደ አለው ሀገር እንዲሄዱ ለመርዳት ነው።

በረራ ወደ መቆያ ቦታዎች የተገደቡ ናቸው እንዲሁም ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወይም አፋጣኝ የከለላ ፍላጎት ያላቸውን ስደተኞች ለመቀበል ፈቃደኛ በሆኑ በሶስተኛ ሀገሮች ይወሰናሉ። ምንም እንኳን UNHCR ያለማቋረጥ ጥገኝነት ጠያቂዎችን እና ስደተኞች በዘፈቀደ እስራት እንዲፈቱ ቢጠይቅም በእስር ላይ መሆን ማለት ለእነዚህ በረራዎች ቅድሚያ ይሰጥዎታል ማለት አይደለም።

በረራ ወደ መቆያ እንዲሄዱ የተመረጡት ሰዎች ከትውልድ ሀገርዎ ለቀው እንዲወጡ ስላደረጋችሁ ሁኔታ እና በሊቢያ ስላላችሁበት ሁኔታ በUNHCR ሰራተኞች ቃለ መጠይቅ ይደረጋል። በረራ ወደ መቆያ ለመሄድ መመረጥ ወይም አለመመረጥ የሚወሰነው በተቀባይ ሀገራት መንግስታት ውሳኔ ሆኖ ያሉበትን ሁኔታ ከግንዛቤ ውስጥ ያስገባሉ።

እባክዎን ያስተውሉ ሁሉም የ UNHCR አገልግሎቶች በረራ ወደ ማቆያ ቦታዎችን ጨምሮ ነፃ ናቸው፤ ምንም አይነት ክፍያ አይጠየቅም።

ወደ ሶስተኛ ሀገር መልሶ ማቋቋም ምንድን ነው? የመልሶ ማቋቋም መስፈርቶች ምንድ ናቸው?

UNHCR የመጨረሻ ግብ ስደተኞች ህይወታቸውን በክብር እና በደህንነት እንዲገነቡ የሚያስችል የረጅም ጊዜ (ወይም “ቋሚ”) መፍትሄዎችን ማግኘት ነው። እነዚህ መፍትሄዎች በፈቃደኝነት ወደ አገር ቤት መመለስ፣ የአካባቢ ውህደት ወይም ወደ ሶስተኛ ሀገር መልሶ ማቋቋም ሊሆኑ ይችላሉ።

ወደ ሶስተኛ ሀገር መልሶ ማቋቋም ማለት ስደተኞችን መምረጥ እና ከለላ ከጠየቁበት ልትቀበላቸው ፍቃደኛ ወደ ሆነች ሀገር ማሻገር እና በመጨረሻም ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ማግኘትን ያካትታል ። ወደ ሶስተኛ ሀገር መልሶ መቋቋም መብት አይደለም ። የተለየ ከለላ የሚያስፈልጋቸው እና በአንድ ወይም ከዚያ በላይ በሆነ UNHCR ወደ ሶስተኛ ሀገር መልሶ ማቋቋም መስፈርት ምድቦች ስር ለወደቁ ብቻ ነው።

UNHCR ጋር መመዝገብ ማለት በቀጥታ ወደ ሶስተኛ ሀገር መልሶ ማቋቋም ግምት ውስጥ ትገባላቹ ወይም አመልክታችኋል ማለት አይደለም። ከሊቢያም ሆነ ከሌላው ዓለም ጥቂት ቁጥር ያላቸው ስደተኞች ብቻ ናቸው ወደ ሶስተኛ ሀገር መልሶ ማቋቋም የተቻለው። ስደተኛን ወደ ወደ ሶስተኛ ሀገር መልሶ ማቋቋም የመጨረሻ ውሳኔ የሚወሰነው በተቀባዩ ሀገር እንጂ በ UNHCR አይደለም።

በረራ ወደ ማቆያ ቦታዎችን ወይም ሶስተኛ ሀገር መልሶ ማቋቋም ቃለ መጠይቅ እንዲደረግልኝ እንዴት እጠይቃለሁ?

አንዴ በUNHCR ከተመዘገቡ በኋላ በUNHCR ከለላ ስር ባለ ጉዳይ መሆንዎን የሚያረጋግጥ የ UNHCR ሰርተፍኬት ይሰጥዎታል ። መመዝገብ በረራ ወደ ማቆያ ቦታ ወይም ወደ ሶስተኛ ሀገር መልሶ መቋቋም ግምት ውስጥ ለመግባት የመጀመሪያው እርምጃ ነው።

ጥገኝነት ጠያቂዎች እና ስደተኞች በረራ ወደ ማቆያ ቦታ ወይም ውደ ሶስተኛ ሀገር መልሶ መቋቋም በራሳቸው ማመልከት አይችሉም። UNHCR በሦስተኛ ሀገራት በሚሰጡት ዕድሎች ውስንነት ምክንያት በጣም ተጋላጭ ናቸው ተብሎ የተለዩ፤ ለቃለ መጠይቅ የሚጠሩት በረራ ወደ ማቆያ ቦታ ወይም ውደ ሶስተኛ ሀገር መልሶ መቋቋም መስፈርቱ ውስጥ የገቡት ብቻ ናቸው ።

በUNHCR ከበርካታ አመታት ጀምሮ ተመዝግቤያለሁ ነገር ግን ማንም በረራ ወደ ማቆያ ቦታዎችን ወይም ሶስተኛ ሀገር መልሶ ማቋቋም ለሚደረግ ቃለ መጠይቅ የጠራኝ የለም። ለምንድነው?

በሶስተኛ ሀገራት በተሰጠዉ ውስን ዕድል ምክንያት ለቃለመጠይቅ የሚጠሩት በጣም ተጋላጭ ተብለው የተለዩ እና በረራ ወደ ማቆያ ቦታዎችን ወይም ሶስተኛ ሀገር መልሶ ማቋቋም መስፈርት የሚያሟሉ ብቻ ናቸው።

UNHCR እርስዎን ለማግኘት ሞክሮ ሊሆን ይችላል ነገር ግን ሊያገኝዎ አልቻለም። በስልክ ቁጥሮችዎ ላይ ስለሚደረጉ ማናቸውም ለውጦች UNHCR ማሳወቅ አስፈላጊ ነው። ቁጥርዎ ከተቀየረ እባክዎን የኤስኤምኤስ፣ የዋትስአፕ ወይም የቫይበር መልእክት ወደ መመዝገቢያ መስመር 📞 0911633466 UNHCR ኬዝ ቁጥርዎን፣ የዘመነውን ስልክ ቁጥርዎን እና አድራሻዎን ጨምሮ ይላኩ።

በረራ ወደ ማቆያ ቦታዎችን ወይም ሶስተኛ ሀገር መልሶ ማቋቋም ያደረግኩትን ቃለ መጠይቁን ውጤት እንዴት ማረጋገጥ እችላለሁ?

ከUNHCR ጋር ቃለ መጠይቅ ካደረጉ እና የቃለ መጠይቁ ውጤት እስካሁን ካላወቁ፤ ይህ ማለት የእርስዎ ጉዳይ አሁንም ገና እየታየ ነው ማለት ነው። UNHCR ውሳኔ ላይ ሲደርስ ወይም አስፈላጊ ከሆነ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያነጋግርዎታል።

እባኮትን ይታገሱ እንዲሁም UNHCR ትክክለኛ ስልክ ቁጥርዎ እንዳለው ያረጋግጡ።

የስልክ ቁጥሬ ከተለወጠ ለ UNHCR ማሳወቅ አለብኝ?

አዎ! UNHCR አዲሱን አድራሻዎን መያዙ በጣም አስፈላጊ ነው።

የአድራሻ ቁጥርዎ ከተቀየረ እባኮትን የኤስኤምኤስ፣ የዋትስአፕ ወይም የቫይበር መልእክት ወደ መመዝገቢያ የስልክ መስመር 📞 0911633466 ይላኩ UNHCR ኬዝ ቁጥርዎን፣ የዘመነውን ስልክ ቁጥርዎን እና አድራሻዎን ያካትቱ።

የአድራሻ ዝርዝሮችዎ በእኛ የፋይል ጎታ በ7 የስራ ቀናት ውስጥ ይዘመናሉ። መረጃዎ መዘመኑን የሚያረጋግጥ መልእክት ይደርስዎታል።


<< ወደ ሊቢያ መነሻ ገጽ ተመለስ >> በእገዛ ገጻችን ላይ ሌላ አገር ይምረጡ