የገንዘብ እርዳታ

የጥሬ ገንዘብ ድጋፍ  UNHCR ሊቢያ ድጋፍ ከሚሰጥባቸው ጠቃሚ መንግዶች አንዱ ነው:: የገንዘብ ድጋፍ ስደተኞችና ጥገኝነት ፈላጊዎች መሰረታዊ ፍላጎቶቻቸውን እንዲሸፍኑ፣ የቤተሰባቸውን ኑሮ እንዲያሻሽሉ እና ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ደህንነታቸውን ከፍ እንዲል ያስችላል::

UNHCR ከ CESVI እና ከኖርዌይ የስደተኞች ድርጅት (NRC) ጋር በመተባበር በመላ ሊቢያ ውስጥ ለሚገኙ ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች መሰረታዊ ፍላጎቶቻቸውን: ማለትም  የምግብ፣ የውሃ፣ የንፅህና እቃዎች፣ የጤና አጠባበቅ እንዲሁም የቤት ኪራይ ወጪአቸውን እንዲሸፍኑ የሚያግዝ የገንዘብ ድጋፍ ያደርጋል።

CESVI እና NRC ለስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች የገንዘብ ድጋፍ ይሰጣሉ፣ ይህም ለግለሰብ ፍላጎቶች አጠቃላይ ምላሽ አካል ነው። ለገንዘብ ዕርዳታ ብቁነት የሚወሰነው ተጋላጭነትን ጨምሮ በርካታ ሁኔታዎችን ከግምት ውስጥ በሚያስገባ ልዩ ክፍል ነው።

የጥሬ ገንዘብ እርዳታ ያስፈልገኛል። እንዴት መጠየቅ እችላለሁ?

ለስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች የገንዘብ ዕርዳታ የሚሰጠው UNHCR ወይም በአጋራችን CESVI የተጋላጭነት ግምገማዎችን ተከትሎ ብቻ ነው። በUNHCR እና CESVI የተደረጉት ግምገማዎች በከተማ ውስጥ በጣም ተጋላጭ ለሆኑ ግለሰቦች እርዳታ እና ድጋፍ ከማድረግ ጋር የተያያዙ ናቸው። የቃለ መጠይቁ ባህሪ፤ የከለላ ፍላጎቶች ግምገማዎች የሚደረጉት የተወሰኑ የከለላ አደጋ እና ስጋቶች ሲኖሩ ብቻ ነው።

ከዚህ ቀደም ካላደረጉ፣ የUNHCR፣ CESVI ወይም የ Tawasul የስልክ መስመሮችን መደወል ይችላሉ። ከዚህ ቀደም አድርገው ከሆነ እና በእርስዎ ሁኔታ ላይ ምንም አይነት ትልቅ ለውጥ ከሌለ፤ እንደገና ቃለ መጠይቅ አይደረግልዎም።

ለሁለት ወራት ያህል የገንዘብ እርዳታ አግኝቻለሁ ከዚያ በኋላ ግን አላገኘሁም። እንደገና እንዴት ልጠይቅ እችላለሁ?

በልዩ የተጋላጭነት መስፈርት መሰረት ለሚሰጠው የ አጣድፊ ችግር   የገንዘብ እርዳታ አግኝተው ሊሆን ይችላል። ይህ የአደጋ ጊዜ የገንዘብ እርዳታ የሁለት ጊዜ ክፍያ ብቻ ነው።

ከዚህ ቀደም የገንዘብ እርዳታ ከተቀበሉ እና በእርስዎ ሁኔታ ላይ ጉልህ ለውጥ ካለ፣ ለተጨማሪ ድጋፍ የ UNHCR አጋር CESVI የስልክ መስመሮችን በ 📞 0910027717 ወይም 📞 0910027716 (እሑድ እስከ ሐሙስ ከ 09.00 እስከ 17.00) መደወል ይችላሉ።


ተዛማጅ መረጃ፡- << ወደ ሊቢያ መነሻ ገጽ ተመለስ >> በእገዛ ገጻችን ላይ ሌላ አገር ይምረጡ