ከ 18 ዓመትበታችናችሁ?

ከ 18 ዓመት በታች ናችሁ? ከሆናችሁ ይህ ገጽ ለናንተ ነው! አገራቸውን ለቀው ለወጡት እና አሁን በሊቢያ ላሉት ህጻናት እና ወጣቶች ሰለሚሰጡት አገልግሎቶች መረጃ እዚህ ታገኛላችሁ።

ስደተኛ የሚባለው ማነው? 👧🏽👦🏽

ስደተኞች ያልተለመዱ እና ከባድ ጊዜያትን ያሳለፉ ሰዎች ናቸው። በኖሩበት አገር ያጋጠመ ግጭት ወይም ክስ አደጋ ላይ ጥሏቸዋል። ከመሸሽ ሌላ አማራጭ አልነበራቸውም። ስለዚህ ስደተኞች በገዛ አገራቸው ኣይኖሩም እና ቢያንስ አንድ ድንበር አቋርጠዋል። ወደ ሃገራቸው ከተመለሱ  ቀጣይነት ያለው ግጭት ኣደጋ ላይ ሊጥላቸው ይችላል ወይም በብሔራቸው፣ በዘር ወይም በፆታዊ ዝንባሌያቸው ወይም ከሃይማኖት፣ ከማህበራዊ ቡድን ወይም ከፖለቲካዊ አመለካከታቸው ጋር በተያያዘ ጉዳት ሊያደርስባቸው ይችላል። ስደተኞችን ለመጠበቅ የወጡ ኣለምአቀፍ ህጎች አሉ። እና ወደየ አገራቸው መመለስ አደጋ ላይ የሚጥላቸው ከሆነ ወደ አገራቸው ሊላኩ አይችሉም።

በሊቢያ ስላሉት ስደተኞች እና UNHCR የበለጠ ለማወቅ የእኛን ቪዲዮ ማየት ትችላላቹ።

በ UNHCR መመዝገብ/መቅረብ የምችለው እንዴት ነው? 💻🏢👧🏽👦🏽📆

ሊቢያ ውስጥ ከቤተሰባችሁ ጋር የምትኖሩ ከሆነ መጀመሪያ ከወላጆቻችሁ ወይም ከሚታመን ትልቅ ሰው ጋር መነጋገር ጥሩ ሊሆን ይችላል። ነገርግን በራሳችሁ ልታገኙን ከፈለጋችሁም ትችላላችሁ😊። ከእኛ ጋር መመዝገብ ከፈለጋችሁ በመጀመሪያ ቀጠሮ መያዝ ይኖርባችዋል። ወደ ምዝገባ መስመራችንን በ 📱📞091 163 3466 መደወል ትችላላችሁ። Tበመስመሩ ላይ ያለው ሰው ስማችሁን፣ የተወለዳችሁበትን ቀን፣ የተወለዳችሁበትን ቦታ እና ከሀገር የወጣችሁበትን ምክንያት ጨምሮ ጥቂት ጥያቄዎችን ይጠይቃችኋል እና መቼ መመዝገብ እንደምትችሉ አሳውቆ የምዝገባ ቀጠሮ ይሰጣችኋል።

ወደ ቃለ መጠይቁ ሰትመጡ ፓስፖርት፣ መታወቂያ ካርድ፣ የልደት የምስክር ወረቀት፣ ወዘተ ጨምሮ ሰነዶች ካላችሁ ሁሉንም ሰነዶች ይዛቹ መምጣት አለባቹ። ይህ በጣም አስፈላጊ ሂደት ስለሆነ ያላቹን ማንኛውንም ሰነድ ለማቅረብ አትፍሩ። በመመዝገቢያ ገጻችን ላይ ወይም በቪዲዮው ላይ ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ትችላላቹ

በሊቢያ ብቻዬን ነኝ እና እርዳታ እፈልጋለሁ። UNHCR ምን ሊያደርግልኘ ይችላል? 👧🏽👦🏽

በመጀመሪያ በUNHCR መመዝገብ አለባቹ – ይህን እንዴት ማድረግ እንዳለባቹ ከላይ ማየት ትችላላቹ።  አንዴ ይህን ካደረጋቹ እንደአስፈጊነቱ በተለያዩ መንገዶች ልንረዳቹ እንችላለን እና በሊቢያ ስለምንሰጣቸው የተለያዩ የእርዳታ አይነቶች ለማወቅ የእኛን ቪዲዮ ማየት ትችላላቹ እናም የአገልግሎቶቹን ዝርዝር መግለጫ እዚህ ማንበብ ትችላላቹ። ከታች ከተዘረዘሩት የስልክ መስመሮች ውስጥ በአንዱ ልታነጋግሩን እና ያላቹበትን ሁኔታ እና ምን ዓይነት እርዳታ እንደሚያስፈልጋቹ ታስረዱን እና ምን ማድረግ እንዳለባቹ እንነግራቿለን። መደወል የምትችሉባቸው ቁጥሮች እነሆ፡-

📱📞የዩኤንኤችአር ምዝገባ ስልክ ቁጥር፡ 091 163 3466 (ከእሁድ እስከ ሐሙስ 08:30-16:30)

📱📞 የዩኤንኤችአር ጥበቃ የስልክ መስመር፡ 091 712 7644 (ከእሁድ እስከ ሐሙስ 08:30-16:30)

📱📞 የታዋሱል የጋራ ግብረመልስ መንገድ የስልክ መስመር፡ 1404 (ከእሁድ እስከ ሐሙስ 09:00-23:00) – በሰብአዊ ፕሮግራሞች ላይ መረጃ ለማግኘት፣ ቅሬታቹን ለማሰማት እና ግብረ መልስ ለመስጠት ለናንተ የተዘጋጀ ከክፍያ ነጻ የሆነ ሀገር አቀፍ የስልክ መስመር ነው። እንደአስፈላጊነቱ፣ ወደ ሚመለከታቸው የሰብአዊ ድርጅቶችም ልትመሩ ትችላላቹ።

📱📞 CESVI የስልክ መስመር፡ 091 002 7717 ወይም 092 276 7166 (ከእሁድ እስከ ሐሙስ 09:00-17:00) – CESVI እንደ እናንተ ካሉ ልጆች ጋር በሊቢያ ውስጥ የሚገኙትን ጨምሮ እርዳታ ከሚያስፈልጋቸው ሰዎች ጋር ከሚሰሩ አጋሮቻችን አንዱ ነው።

እኔ በሊቢያ ውስጥ ብቻዬን የምኖር ልጅ ነኝ፣ ነገር ግን መቀላቀል የምፈልጋቸው በሌላ አገር ውስጥ ያሉ የቤተሰብ አባላት አሉኝ። UNHCR ሊረዳኝ ይችላል? 🌍✈️

አንድ ልጅ በተቻለ መጠን ከቤተሰቡ ጋር አብሮ መሆኑ አስፈላጊ ነው።  UNHCRን ካነጋገራቹ፣ እናንተን ለመርዳት የተቻለንን እናደርጋለን። ቤተሰቦቻቹን ለማግኘት እና ግንኙነት ለመመስረት እንሞክራለን። እንዲሁም ከቤተሰቦቻቹ ጋር ለማገናኘት እንሞክራለን; ይሁን እንጂ ሂደቱ ከአገር አገር ይለያያል። እባካቹ በUNHCR ጥበቃ የስልክ መስመር 📱📞 091 712 7644 ኣግኙን።  እንዲሁም ተጨማሪ መረጃ ➡️እዚህ ማግኘት ይችላሉ።

አንድ ሰው ጎድቶኛል፣ ወይም እንዳይጎዳኝ እፈራለሁ። ምን ላደርግ እችላለው? 

ማንም ሰው ማንኛውንም ህጻን የመበደል፣ የችላ የማለት ወይም የመጉዳት መብት የለውም – ወላጆቹ፣ ዘመዶቻቸው ወይም አስተማሪዎችን ጨምሮ። አንድ ሰው የጎዳቹ ከሆነ ወይም ምቾት በሚነሳ መንገድ ከነካቹ ወይም ጉዳት ያደርሰብኛል ብላቹ ከፈራቹ ሊረዷቹ የሚችሉ ድርጅቶች አሉ። UNHCRን ካነጋገራቹ፣ እናንተን ለመርዳት የተቻለንን እናደርጋለን። በሚከተሉት ቁጥሮች ልታገኙን ትችላላቹ።

📱📞የዩኤንኤችአር ጥበቃ የስልክ መስመር፡ 091 712 7644 (ከእሁድ እስከ ሐሙስ 08:30-16:30)

📱📞 CESVI የስልክ መስመር፡ 091 002 7717 ወይም 092 276 7166 (ከእሁድ እስከ ሐሙስ 09:00-17:00)

በአፋጣኝ ዶክተርን እንዲያገኙ የሚጠይቅ ማንኛውንም አይነት ጥቃት ካጋጠማቹ፡ ማነጋገር ትችላላቹ፡-

📱📞 IRC ለጤና እርዳታ፡

የሕክምና ድንገተኛ የስልክ መስመር፡ 091 035 4839 (24/7 – በየቀኑ በማንኛውም ጊዜ)

አሁን ትምህርት ቤት እየሄድኩኝ አደለም, ግን መሄድ እፈልጋለሁ. ወደ ትምህርት ቤት ለመሄድ እርዳታ እንዴት ማግኘት እችላለሁ? 🏫📚

ማንኛውም ህጻን ትምህርት ቤት የመሄድ መብት አለው ። እናም UNHCR ወደ UNCEF በመምራት ሊረዳቹ ይችላል። በእነሱ በኩል፣ እናንተን በህዝብ ትምህርት ቤቶች ወይም መደበኛ ባልሆነ ትምህርት ማለትም በUNCEF  በሚተዳደሩት Baity ማዕከላት  እንድትመዘገቡ መርዳት ይቻል ይሆናል። ከላይ በገለጽነው መንገድ ልታገኙን ትችላላቹ፣ እናም በሂደቱ ውስጥ እንረዳቹዋለን። እባካቹ በ UNHCR ጥበቃ የስልክ መስመር 📱📞 091 712 7644 ኣግኙን።

የአካል ጉዳተኛ ነኘ። ልትረዱኝ ትችላላቹ?

እኛ፣ ከአጋራችን CESVI ጋር፣ አጋዥ መሳሪያዎችን፣ የውጭ አገልግሎት አቅራቢዎችን ሪፈራል፣ የስነ-ልቦና ድጋፍን፣ መሰረታዊ የአካል ማገገሚያ እና በቤት ውስጥ ክትትልን ጨምሮ ልዩ እርዳታ እንሰጣለን። ማንኛውም የአካል ጉዳት ካለባቹ እና እርዳታ ከፈለጋቹ፣ እባካቹ  አጋራችን CESVI ን በስልክ መስመራቸው፡ 📱📞 091 002 7717 ወይም 📱📞 092 276 7166 ያግኙ።

በጉዞዬ ወቅት ያጋጠሙኝ መጥፎ ገጠመኞች አሉ ፣ አዝናለሁ፣ እናደዳለሁ፣ እጨነቃለሁ፣ እፈራለሁ፣ ወይም ግራ እጋባልው። ይህ የተለመደ ነው?

ከአገራችሁ ከወጣቹ እና ብዙ አስፈሪ ነገሮችን ካያቹ ወይም ካጋጠማቹ በኋላ መበሳጨት የተለመደ ነው። ያያቹዋቸውን ወይም ያጋጠሟቹን ነገሮች ከአእምሯቹ ለማውጣት ሊችግር ይችላል። ከምትወዷቸው እና ከምትጨነቁላቸው ሰዎች ልትለዩ እና ወይም ቀጥሎ ምን እንደሚፈጠር በማሰብ ትጨነቁም ይሆናል። ሁሉም ነገር እንገዳ እንደሆነ ሊሰማቹም ይችላል።ይህንን አስቸጋሪ ሁኔታ ለመቋቋም ሊረዷቹ የሚችሉ አንዳንድ ቀላል መንገዶች። ከወላጆቻቹ ጋር ከሆናቹ ወይም በአጠገባቹ የምታምኑት ሰው ካለ ምን እንደሚሰማቹ ተናገሩ።

ከስነ-ልቦና ባለሙያ፣ ከአማካሪ ወይም ከዶክተር እርዳታ ለመጠየቅ ኣታመንቱ – ብዙዎቹ እነዚህ ባለሙያዎች በአገልግሎት አቅራቢዎች በኩል በነጻ ይገኛሉ። የሚሰማቹን ስሜት ለማውራት እርዳታ ያስፈልገናል ብላቹ ካሰባቹ አጋራችንን CESVI በ 📱📞 091 002 7717 ወይም 📱📞 092 276 7166 (ከእሁድ እስከ ሐሙስ 09:00-17:00) ማግኘት ትችላላቹ።

በአፋጣኝ ዶክተርን እንዲያገኙ የሚጠይቅ ማንኛውንም አይነት ጥቃት ካጋጠማቹ፡ ማነጋገር ትችላላቹ፡-

📱📞 IRC ለጤና እርዳታየሕክምና ድንገተኛ የስልክ መስመር፡ 091 035 4839 (24/7 – በየቀኑ በማንኛውም ጊዜ)