ሌሎች ሰብአዊ መብቶችን ለመጠቀም ጤና የማግኘት መብት አስፈላጊ ነው። ይህ መብት መሰረታዊና አካታች መብት ሲሆን: ወቅታዊ እና ተገቢ የጤና እንክብካቤ እና ንፁህ የመጠጥ ውሃ: ንፁህና በቂ የሆነ እንዲሁም ደህንነቱ የተጠበቀ ምግብና የመኖሪያ ቤት አቅርቦት፣ጤናማ የሥራ እና የአካባቢ ሁኔታዎች፣ ከጤና ጋር የተያያዘ ትምህርት እና መረጃ ማግኘት መብቶችን ያጠቃልላል:: UNHCR ከሊቢያ የጤና ባለሙያዎች ጋር ይሰራል እንዲሁም አስፈላጊ የጤና አገልግሎቶችን በበቂ ሁኔታ ለማቅረብ፣ የአካባቢ ጤና አገልግሎቶችን ለማሻሻል እና ስደተኞችን እና ጥገኝነት ጠያቂዎችን በሀገራዊ የጤና ስርአት ውስጥ ለማካተት ከሌሎች የጤና አጋሮች ጋር በጤና የስራ ቡድን በኩል ይሰራል።
አጋራችን ዓለም አቀፍ የነፍስ አድን ኮሚቴ (IRC) ለስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች በትራብሎስ በሚገኘው የማህበረሰብ እርዳታ ማእከል (CDC) እንዲሁም የመጀመሪያ ደረጃ የጤና እንክብካቤ ማእከላት የጤና አገልግሎቶችን ጨምሮ በርካታ አገልግሎቶችን ይሰጣል፡-
አልምጋሪፍ የሕዝብ ጤና ጣቢያ (ረቡዕ ፣ ሐሙስ)
ዛውየትአል-ዲህማኒ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና እንክብካቤ ማዕከል (እሑድ ፣ ሰኞ ፣ ማክሰኞ)
አጋራችን CESVI የስነ-ልቦና እና የአእምሮ ጤና አገልግሎቶች ለሚያስፈልጉአቸው ለስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ይሰጣል። አጋራችን IRC ደግሞ የአእምሮ ጤና ምክክርን ጨምሮ የአእምሮ ጤና እና የስነ-ልቦና-ማህበራዊ ድጋፍ አገልግሎቶችን ይሰጣል።