የጥሬ ገንዘብ ድጋፍ UNHCR ሊቢያ ድጋፍ ከሚሰጥባቸው ጠቃሚ መንግዶች አንዱ ነው:: የገንዘብ ድጋፍ ስደተኞችና ጥገኝነት ፈላጊዎች መሰረታዊ ፍላጎቶቻቸውን እንዲሸፍኑ፣ የቤተሰባቸውን ኑሮ እንዲያሻሽሉ እና ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ደህንነታቸውን ከፍ እንዲል ያስችላል::
UNHCR ከ CESVI እና ከኖርዌይ የስደተኞች ድርጅት (NRC) ጋር በመተባበር በመላ ሊቢያ ውስጥ ለሚገኙ ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች መሰረታዊ ፍላጎቶቻቸውን: ማለትም የምግብ፣ የውሃ፣ የንፅህና እቃዎች፣ የጤና አጠባበቅ እንዲሁም የቤት ኪራይ ወጪአቸውን እንዲሸፍኑ የሚያግዝ የገንዘብ ድጋፍ ያደርጋል።
CESVI እና NRC ለስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች የገንዘብ ድጋፍ ይሰጣሉ፣ ይህም ለግለሰብ ፍላጎቶች አጠቃላይ ምላሽ አካል ነው። ለገንዘብ ዕርዳታ ብቁነት የሚወሰነው ተጋላጭነትን ጨምሮ በርካታ ሁኔታዎችን ከግምት ውስጥ በሚያስገባ ልዩ ክፍል ነው።