UNHCR በዘፈቀደ በእስር ላይ የሚገኙ ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች እንዲፈቱ እና በሊቢያ የዘፈቀደ እስራት እንዲያቆም የበርሊን ስምምነት በመጥቀስ እንዲሁም ከእስር ሌላ አማራጮችን በማዘጋጀት የፍትህ ግምገማ ስርዓት እንዲዘረጋ ጠይቋል። አስቸኳይ የሰብአዊ ፍላጎቶችን ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ UNHCR የህይወት አድን የህክምና እና የሰብአዊ እርዳታን በእስር ቤት ማእከላት ያቀርባል፤ ዓላማውም ሰዎችን ለከለላ ክትትል፣መለየት፣ማረጋገጥ፣የመልቀቅ ቅስቀሳ እና የእስር ሌላ አማራጮችን እንዲያዩ ለማድረግ ነው። የዩኤንኤችአር UNHCR በእስር ቤት ማእከላት የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች የሊቢያን የእስር ፖሊሲ ድጋፍ አይወክልም።
በአሁኑ ጊዜ በእስር ቤት ታስሬያለሁ። UNHCR ከእስር እንድፈታ ሊከራከር ይችላል?
UNHCR በዘፈቀደ የታሰሩ ሁሉንም ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎችን እንዲፈቱ ይጠይቃል። UNHCR ህገ-ወጥ ስደትን የመከላከል ዳይሬክቶሬት (DCIM) ስር በኩል ይፋዊ የእስር ቤት ማእከላት ጉብኝት ያደርጋል። በአስር ቤት ተቋማቱ UNHCR እና አጋሮቹ የህክምና ርዳታ መስጠትን፣ የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን፣ ሌሎች መሰረታዊ የእርዳታ ቁሳቁሶችን ማሰራጨትን ጨምሮ ህይወት አድን እርዳታ ይሰጣሉ።
በአሁኑ ጊዜ በእስር ቤት ታስሬያለሁ፣ እና በUNHCR መመዝገብ እፈልጋለሁ። ምን ላድርግ?
UNHCR በማቆያ ማእከላት የምዝገባ ስራዎችን አያከናውንም። ሆኖም UNHCR እንድትፈቱ ይከራከራል ከተለቀቁ በኋላ ደግሞ የምዝገባ ቀጠሮ ይሰጥዎታል።
ከታሰረው ዘመዴ ጋር ያለኝ ግንኙነት ጠፋ። እሱን/እሷን እንዳገኛት ልትረዱኝ ትችላላችሁ?
ወደ UNHCR ከለላ(Protection) የስልክ መስመር 0917127644 በመደወል ስለ ዘመድዎ ዝርዝር መረጃ መስጠት ይችላሉ።
UNHCR የሚፈለጉትን ሰው እንዲያገኙ በህገወጥ ስደት መከላከል ዳይሬክቶሬት (DCIM) ስር ይፋዊ የማቆያ ማእከላት ጉብኝት ያደርጋል።
UNHCR ዘመድዎን ሲያገኝ እና ዘመድዎ ፈቃዱን ከሰጠ፣ እርስዎን ያገኝዎታል።