የውሸት መረጃ ማንቂያ

UNHCR ሊቢያ በአሁኑ ጊዜ በማህበረሰቡ ውስጥ እየተሰራጨ ያለውን የውሸት መረጃ ያውቃል፣ ከእነዚህም መካከል:

🔴 20,000 ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሌላ ሀገር ለማጓጓዝ ሁለት የክሩዝ መርከቦች ትሪፖሊ ገብተዋል የሚለው UNHCR እጁ አለበት በሚል መረጃ የሃሰት ወሬ ነዉ።

🔴 በዋትስአፕ የተሰራጨ የተጭበረበረ መልእክት በኦንላይን ለመመዝገቢያ ሊንክ እየተባለ ላለዉና ከUNHCR 1,300 ዲናር የገንዘብ ድጋፍ እንደሚደረግ የሚለዉ የዉሸት ቃል ነዉ።

⚠️ ሁለቱም ከላይ የተጠቀሱት የሐሰት መልእክት ናቸዉ።

UNHCR እንደዚህ አይነት እንቅስቃሴዎችን እያመቻቸ አይደለም። እናም ምንም አይነት የክሩዝ መርከቦች ለዚህ አላማ ወደዚህ አልመጡም።

UNHCR በኦንላይን ግንኙነቶችን ጨምሮ ምንም አይነት የገንዘብ ድጋፍ አይሰጥም።

UNHCR እና አጋሮቹ ሁሉንም አገልግሎቶች በነጻ ነዉ የሚሰጡት ከለላ/ጥበቃ ፤ እርዳታ እና ማንኛዉም መረጃ- ከክፍያ ነጻ።

🛑 የግል መረጃችሁን ወይም ሰነዶችን ይፋ ባልሆኑ ግንኙነቶች ወይም ከUNHCR ነን ለሚሉ ግለሰቦች አታጋሩ።

➡️ ሁሌም በኦፌሻላዊ የግንኙነት ቻናሎቻችን ላይ ተከታተሉን።
✅ ከUNHCR በቀጥታ ካልሰማችሁ አትመኑ።