ጥገኝነት ለማግኘት እንዴት ማመልከት እንደሚቻል። ወደ ስዊድን የሚገቡት ወደ አንድ የመግቢያ ወደብ (አውሮፕላን ማረፊያ፣ የመሬት ድንበር መሻገሪያ ወይም የባህር ወደብ) በኩል ከሆነ፣ ለድንበር ፖሊስ ጥገኝነት መጠየቅ እንደሚፈልጉ ይንገሩ። የድንበር ፖሊስ አንዳንድ ጥያቄዎችን ይጠይቅዎታል፣ እንዲሁም ማመልከቻዎን ወደሚያስገቡበት የስዊድን የስደተኞች ኤጄንሲ ይልክልዎታል።
ቀድሞውኑ በስዊድን ውስጥ ከሆኑ እና ጥገኝነት ለመጠየቅ ከፈለጉ በስዊድን የስደተኞች ኤጄንሲን ስቶክሆልም፣ ጎተንበርግ እና ማልሞ በሚገኙ ቢሮዎቻቸው ውስጥ ማነጋገር አለብዎት። የስዊድን የስደተኞች ኤጀኢንሲ ድህረ-ገጽ ላይ ስለ እነዚህ ቢሮዎች አድራሻዎች እና የስራ ሰዓቶች ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ (በማጣሪያ ምናሌ ውስጥ “ለጥገኘት ያመልክቱ” የሚለውን ይምረጡ።) ጥገኝነት ለመጠየቅ ቀጠሮ መያዝ አያስፈልግዎትም።
እንዲሁም በስዊድን ውስጥ ለጥገኝነት እንዴት እንደሚያመለክቱ በስዊድን የስደተኞች ኤጄንሲ ድህረ-ገጽ ላይ ተጨማሪ መረጃ በአማርኛ፣ በአረብኛ፣ በዳሪ፣ በፋርሲ፣ በፈረንሳይኛ፣ በእንግሊዝኛ፣ በኩርማንጂ፣ በፓሽቶ፣ በሩሲያኛ፣ በሶማሊኛ፣ በሶራኒ፣ በስፓኒሽ፣ በስዊድንኛ፣ ትግርኛ እና ቱርክኛ ቋንቋዎች ያገኛሉ።
የስዊድን ባለሥልጣናት የጥገኝነት አሰራርን የሚመለከቱ ጉዳዮች በብሔራዊ ህግጋትና ደንቦች መሰረት እና በጥገኝነት ጉዳዮች ላይ ልዩ ስልጠና በወሰዱ እና ብቃት ባላቸው ብሔራዊ ባለሥልጣናት ይመራሉ።
UNHCR በስዊድን ውስጥ የጥገኝነት ማመልከቻዎችን በማስኬድ ሂደት ውስጥ አይሳተፍም።