የአደጋ ጊዜ አገልግሎቶች ለስዊድን ፖሊስ፣ ለነፍስ አድን አገልግሎትና ለእሳት አደጋ መከላከያ እንዲሁም ለአስቸኳይ ራስን የማጥፋት አደጋ ለሚጋለጡ ሰዎች የጋራ የአደጋ ጊዜ ቁጥር 📞 112 ነው። ለድንገተኛ ጊዜ ጥሪዎች በ 📞112 ይደውሉ። በአስቸኳይ ጉዳዮች ለፖሊስ ለመደወል በ 📞 112 ይደውሉ። አጠቃላይ መረጃ ከፖሊስ ለማግኘት በ 📞 114 14 ይደውሉ። የድንገተኛ ጊዜ ህክምና አገልግሎቶችን ለማግኘት በ 📞 112 ይደውሉ። አጠቃላይ የሕክምና ምክር ለማግኘት ወደ 📞1177 በመደወል Vårdguidenን ያነጋግሩ። የእሳት አደጋ መከላከያ መምሪያን ለማግኘት በ 📞 112 ይደውሉ።