ለጥገኝነት ካመለከትኩ በኋላ ምን ይከሰታል

ደረጃ 1 – ምዝገባ

የጥገኝነት ማመልከቻን ካስገቡ በኋላ፣ የስዊድን የስደተኞች ኤጄንሲ በደብሊን ደንብ መሰረት፣ የትኛው ሀገር የጥገኝነት ማመልከቻዎን የማስተናገድ ሃላፊነት እንዳለበት ይገመግማል።

ስዊድን የጥገኝነት ማመልከቻዎን የማስተናገድ ሃላፊነት ካለባት፣ የስዊድን የስደተኞች ኤጄንሲ የጥገኝነት ማመልከቻዎን መገምገሙን ይቀጥላል። የስዊድን የስደተኞች ኤጄንሲ በስዊድን ውስጥ ጥበቃ የማግኘት መብት እንዳለዎ እስኪወስን ድረስ በስዊድን ውስጥ መቆየት ይችላሉ።

ማመልከቻዎ ከተመዘገበ በኋላ፣ የመጨረሻ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ የጥገኝነት ጠያቂነት ሁኔታ ይኖርዎታል። እንዲሁም ኤልኤምኤ ካርድ ተብሎ የሚጠራው ይደርስዎታል። ካርዱ የመታወቂያ ካርድ ሳይሆን፣ ጥገኝነት ጠያቂ መሆንዎን እና ውሳኔን እየጠበቁ በስዊድን ውስጥ እንዲቆዩ የተፈቀደልዎ መሆንዎን የሚያሳይ የምስክር ወረቀት ነው።

የምስክር ወረቀት (AT-UND ተብሎ የሚጠራው) የሥራ ፈቃድ እንዲኖሮት የማይገደዱ መሆኑን ሲያሳይ በስዊድን ውስጥ እንደ ጥገኝነት ጠያቂ ሆነው መሥራት ይችላሉ፤

የራስዎን ገንዘብ ሰርተው የማያገኙ እና በስዊድን ውስጥ እራስዎን ማስተዳደር የማይችሉ ከሆነ፣ ለስዊድን የስደተኞች ኤጄንሲ የገንዘብ ድጋፍ ለማግኘት ማመልከት ይችላሉ።

የሚኖሩበት ቦታ ከሌለ የስዊድን የስደተኞች ኤጄንሲ ማረፊያ ሊያዘጋጅልዎ ይችላል። በተጨማሪም በራስዎ የመኖሪያ ቦታ ማመቻቸት ይችላሉ።

እንደዚህ አይነት አገልግሎቶችን እንዴት ማግኘት እንደሚቻል ተጨማሪ መረጃ በስዊድን የስደተኞች ኤጄንሲ ድህረ-ገጽ ላይ በእንግሊዝኛ እና በስዊድንኛ ይገኛል።

ደረጃ 2 – ቃለ መጠይቅ

በስዊድን ውስጥ ጥገኝነት የጠየቁበትን ምክንያቶች ከስዊድን የስደተኞች ኤጄንሲ ሰራተኛ ጋር በሚደረግ የግለሰብ ቃለ መጠይቅ ላይ ለማብራራት እድል ይሰጥዎታል። የጥገኝነት ቃለ መጠይቁ በጥገኝነት አሰጣጥ አሰራር ውስጥ በጣም አስፈላጊ እርምጃ ነው። በቃለ መጠይቁ ወቅት፣ የጥገኝነት ማመልከቻዎን ለመደገፍ በተቻለ መጠን ብዙ መረጃዎችን ለማቅረብ እና ሁሉንም የጥገኝነት ማመልከቻ የሚደግፉ ሰነዶችን ለማቅረብ ዕድሉ አለዎት። ወደ ትውልድ ሀገርዎ ከተመለሱ ያጋጠሙዎትን እና የሚፈሩትን ነገር ሙሉ መግለጫ መስጠት አስፈላጊ ነው። ልዩ ፍላጎቶች ካልዎት፣ በቃለ መጠይቅዎ ወቅት በማንኛውም ጊዜ ያለ ችግር መግለፅ እና የባለሞያ ልዩ ድጋፍን መጠየቅ ይችላሉ። አስተርጓሚ የሚያስፈልግዎት ከሆነ መጠየቅ ይችላሉ።

ለጥገኝነት ማመልከቻዎ (ሰነዶች፣ ከእርስዎ ጋር የጥገኝነት ቃለ-መጠይቅ በሚያደርጉበት ጊዜ ቅጂዎች) ያቀረቡት መረጃ ሁሉ በስዊድን ባለስልጣናት ለትውልድ ሀገርዎ ወይም ለሌላ ለማንም አይጋራም።

ደረጃ 3 – ውሳኔ

በእኔ ጉዳይ ላይ ውሳኔው ምን ሊሆን ይችላል?

ውሳኔው ከተሰጠ በኋላ፣ የስዊድን የስደተኞች ኤጄንሲ እርስዎ ባቀረቡት አድራሻ አማካኝነት፣ ስለ ጥገኝነት ማመልከቻዎ ውጤት መረጃ ይሰጥዎታል።

በወረቀት ላይ የሚደርሰዎት ውሳኔ በስዊድንኛ የተጻፈ ይሆናል፣ ነገር ግን እርስዎ በሚረዱት ቋንቋ በአስተርጓሚ አማካይነት ስለ ውሳኔው በቃል መረጃ ያገኛሉ።

የጥገኝነት አሰራር ሂደት አራት ሊሆኑ የሚችሉ ውጤቶች አሉት፦

  • እርስዎ እንደ ስደተኛ እውቅና ያገኙ እና የመጀመሪያ ጊዜ ለ3 ዓመታት የሚቆይ ጊዜያዊ የመኖሪያ ፈቃድ የተሰጠዎት ይህም ለ2 ዓመት ጊዜዎች በየጊዜው ሊራዘም ይችላል።
  • እንደ ስደተኛ ለመሆን ብቁ ላልሆኑት የሚሰጠው ጥበቃ ተሰጥቶዎታል እና ለ13 ወራት የመጀመሪያ ጊዜ የሚቆይ ጊዜያዊ የመኖሪያ ፈቃድ ተሰጥቶዎታል፣ ይህም ለ 2 ዓመት ጊዜ ሊራዘም ይችላል።
  • የመኖሪያ ፈቃድ የተሰጥዎት በልዩ/በተለይ አስጨናቂ ሁኔታዎች ምክንያት በመጀመሪያ ለ13 ወራት የሚቆይ ሲሆን ይህም ለ2 ዓመት ሊራዘም ይችላል።
  • የጥገኝነት ማመልከቻዎ ውድቅ ተደርጓል።

ጥገኝነት (የመጀመሪያዎቹ ሶስት ውጤቶች ማለትም የስደተኛ ሁኔታ፣ እንደ ስደተኛ ለመሆን ብቁ ላልሆኑት የሚሰጠው ጥበቃ ወይም በልዩ ሁኔታ/ በተለይም በአስጨናቂ ሁኔታዎች ምክንያት የመኖሪያ ፈቃድ) እውቅና ከተሰጠዎት፣ እንደ ስዊድናዊ ዜጎች እኩል በስዊድን ውስጥ የመኖር እና የመሥራት መብት አለዎት። የመኖሪያ ፈቃድዎን ለማረጋገጥ፣ የስዊድን የስደተኞች ኤጄንሲ የመኖሪያ ፈቃድ ካርድ ይሰጥዎታል።

ጊዜያዊ የመኖሪያ ፈቃድ ከተቀበሉ በኋላ፣ በስዊድን የግብር ኤጀንሲ ድህረ-ገጽ ላይ በተቻለ ፍጥነት በስዊድን የግብር ኤጀንሲ በሕዝብ መዝገብ ውስጥ መመዝገብ አለብዎት። የስዊድን የማህበራዊ ዋስትና ስርዓት ጥቅማጥቅሞችን መብት ለማግኘት እና የስዊድን ቋንቋ ኮርሶችን ለመከታተል ምዝገባ አስፈላጊ ነው። በሕዝብ መዝገብ ቤት ከተመዘገቡ በኋላ፣ የስዊድን መታወቂያ ካርድ ለማግኘት ማመልከት ይችላሉ።

ጥገኝነት ለማግኘት ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ ከሆነ በስዊድን የስደተኞች ኤጄንሲ ውሳኔ ከተስማሙ “የመቀበል መግለጫ” መፈረም ይችላሉ። በስዊድን የስደተኞች ኤጄንሲ ውሳኔ ካልተስማሙ፣ ውሳኔውን ይግባኝ ማለት ይችላሉ።



Related information