አሉታዊ ውሳኔን እንዴት ይግባኝ ማለት እችላለሁ?

የጥገኝነት ማመልከቻዎ ውድቅ ከተደረገ፣ ለስደተኞች ፍርድ ቤት ይግባኝ የማስገባት መብት አለዎት። የመኖሪያ ፈቃድ ቢሰጥዎትም በተሰጠው ሁኔታ ዓይነት ካልተስማሙም ይግባኝ የማለት መብት አለዎት።

ውሳኔውን ለመቃወም ይግባኝዎን ለስዊድን የስደተኞች ኤጄንሲ ማቅረብ ይኖርብዎታል፤ እሱም ይግባኝዎን ወደ የስደተኞች ጉዳይ ፍርድ ቤት ያስተላልፋል። ነገር ግን፣ ይግባኙን ለስተኞች ፍርድ ቤት ከማቅረቡ በፊት፣ የስዊድን የስደተኞች ኤጄንሲ ውሳኔውን እንደገና ሊያስብበት ይችላል።

ጠበቃ ካለዎት፣ ጠበቃዎ ይግባኝ ለማቅረብ ሊረዳዎ ይችላል። ጠበቃ ከሌለዎት የስዊድን የስደተኞች ህግ ማዕከልን ማነጋገር ይችላሉ። ይግባኝዎ ከስዊድን የስደተኞች ኤጄንሲ ውሳኔ ከተቀበሉበት ቀን ጀምሮ ባሉት 3 ሳምንታት ውስጥ መቅረብ እንዳለበት ልብ ይበሉ። ስለ ይግባኝ አሰራር ሂደት እና ቀነ-ገደቦች የበለጠ መረጃ ለማግኘት እባክዎን የስዊድን የስደተኞች ኤጄንሲ ድህረ ገጽን ይጎብኙ።

የስደተኞች ጉዳይ ፍርድ ቤት በስዊድን የስደተኞች ኤጄንሲ የተሰጠውን ውሳኔ ሊለውጥ ወይም ሊያረጋግጥ ይችላል። የስደተኞች ጉዳይ ፍርድ ቤት በስዊድን የስደተኞች ኤጄንሲ የተሰጠውን አሉታዊ ውሳኔ የሚያረጋግጥ ከሆነ፣ አሁንም ቢሆን ወደ የስደተኞች ጉዳይ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ይግባኝ ማለት ይችላሉ።

የስዊድን የስደተኞች ኤጄንሲ ወይም የስዊድን ፍርድ ቤቶች የመጨረሻ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ በስዊድን ውስጥ ጥገኝነት ጠያቂነት ሁኔታ የመቆየት መብት አለዎት።

ይግባኝዎ በሁሉም ደረጃዎች ላይ ካልተሳካ ከስዊድን መውጣት ይኖርብዎታል። ወደ ትውልድ ሀገርዎ ለመመለስ እርዳታ ከፈለጉ የስዊድን የስደተኞች ኤጄንሲን ማነጋገር ይችላሉ።

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፣ የስዊድን የስደተኞች ኤጄንሲ ድህረ-ገጽን ይጎብኙ።



Related information