ከ18 ዓመት በታች የሆነ ልጅ ያለ ወላጆቹ ብቻውን ወደ ኖርዌይ ከገባ እና ጥገኝነት ከጠየቀ፣ ሕፃኑ ብቻውን የመጣ ለአካለ መጠን ያልደረሰ ጥገኝነት ጠያቂ ይባላል። ብቻውን የመጣ ለአካለ መጠን ያልደረሰ ጥገኝነት ጠያቂ ልዩ መብቶች አሉት።
➡️በኖርዌይ ውስጥ ብቻቸውን የሆኑ ሕፃናት ስለሚኖራቸው መብቶች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እባክዎ በAsylbarn.no ላይ ያንብቡ።.
➡️በUDI.no ላይ፣ ከዩክሬን ብቻቸውን የመጡ ለአካለ መጠን ያልደረሱ እንዴት ጥገኝነት መጠየቅ እንደሚችሉ ማወቅ ይችላሉ
ብቻቸውን የመጡ ለአካለ መጠን ያልደረሱ በኖርዌይ ውስጥ ተወካይ የማግኘት መብት አላቸው። ተወካይ ማለት ወላጆቹ አብረውት ስላልሆኑ ልጁን ወክሎ የሚንቀሳቀስ አዋቂ ሰው ነው። ተወካዩ በኖርዌይ ውስጥ ብቻቸውን የሆኑ ለአካለ መጠን ያልደረሱ ሕጻናት መብቶችን በተመለከተ የህግ እና የገንዘብ ድጋፍ ይከታተላል።
➡️ብቻቸውን ለሆኑ ለአካለ መጠን ያልደረሱ ጥገኝነት ጠያቂዎች ተወካዮች በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እዚህ ይጫኑ።
ተወካዩ የሚከተሉትን ለማድረግ ይረዳዎታል፦
- በኖርዌይ ኢሚግሬሽን ዳይሬክቶሬት (UDI) ውስጥ ያለውን የጥገኝነት ሂደት ለመረዳት
- የኖርዌይ ባለሥልጣናትን ለማነጋገር
- ሃሳብዎን መግለጽ መቻልዎን ለማረጋገጥ
- ተገቢውን እንክብካቤ እና የጤና እንክብካቤ ማግኘትዎን ለማረጋገጥ
- የሚቆዩበት/የሚኖሩበት ቦታ እንዳገኙ ለማረጋገጥ
- ወደ ትምህርት ቤት ለመሄድ እንደተፈቀደልዎ ለማረጋገጥ