ከጥገኝነት ቃለ መጠይቁ በኋላ ምን ውሳኔ ይደረጋል?

➡️ ጥገኝነት ለማግኘት ያስገቡት ማመልከቻ ተቀባይነት ካገኘ (ለምሳሌ “አዎ” የሚል መልስ ካገኙ)

  • ከኖርዌይ ኢሚግሬሽን ዳይሬክቶሬት (UDI) ደብዳቤ ይደርስዎታል። ደብዳቤው በኖርዌይ ውስጥ ጥበቃ (ጥገኝነት) እንደተሰጠዎት ይገልጻል።
  • በኖርዌይ ውስጥ እንደ ስደተኛ ያለዎት መብቶች እና ግዴታዎች በUDI ደብዳቤ ውስጥ ይብራራሉ።
  • ፖሊስ የመኖሪያ ካርድዎን እና የጉዞ ሰነድዎን ለመልቀቅ ቀጠሮ ለማስያዝ ያነጋግርዎታል። እንዲሁም የግል መታወቂያ ቁጥር ይሰጥዎታል።
  • በኖርዌይ ውስጥ ለመኖር የተሰጠዎት የመኖሪያ ፈቃድ ውሳኔው ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ለአምስት ዓመታት ይቆያል። ይህ ማለት የአምስት ዓመቱ ጊዜ ሲጠናቀቅ ለእድሳት ወይም ለቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ማመልከት አለብዎት ማለት ነው። አምስት ዓመቱ ከመጠናቀቁ በፊት ይህን አስመልክቶ ማሳሰቢያ  ወይም አስታዋሽ ይደርስዎታል።
  • በየትኛው ከተማ ውስጥ እንደሚኖሩ መረጃን ይጠብቃሉ።
  • ወደ ከተማው ለመዛወር ጊዜው ሲደርስ መረጃ ይሰጥዎታል እንዲሁም ለመዛወር እርዳታ ያገኛሉ።
  • በኖርዌይ ውስጥ የመሥራት መብት አለዎት።
  • የኖርዌይ ቋንቋ እና የማህበረሰብ ጥናቶች ኮርሶችን የመከታተል መብት እና ግዴታ አልዎት። እነዚህን ኮርሶች መቼ መጀመር እንደሚችሉ ይነገርዎታል።
  • በኖርዌይ ውስጥ ህጉን መከተል እና መታዘዝ አለብዎት። ይህን ካላደረጉ የመኖሪያ ፈቃድዎ ላይ አሉታዊ መዘዞች ሊያስከትሉ ይችላሉ።

➡️ የጥገኝነት ማመልከቻዎ ውድቅ ከተደረገ (ለምሳሌ “አይ” የሚል መልእክት ካገኙ)

  • አንድ የተሾመ ጠበቃ አሉታዊ ውሳኔውን ያሳውቅዎታል።
  • በውሳኔው ይግባኝ ማለት ይችላሉ። በዚህ ጊዜ ጠበቃው በUDI ውሳኔ ላይ ይግባኝ ለማቅረብ ይረዳዎታል።
  • የይግባኝ ጥያቄዎ ምላሽ እስኪያገኝ ድረስ በኖርዌይ ውስጥ ለመቆየት UDIን መጠየቅ ይችላሉ። UDI ከተስማማ፣ የጥገኝነት ጥያቄዎን በተመለከተ የመጨረሻ ውሳኔ እና መልስ እስኪያገኙ ድረስ በኖርዌይ ውስጥ ይቆያሉ።

< ተመለስ፡ በኖርዌይ ውስጥ ጥገኝነት ለማግኘት እንዴት ማመልከት እንደሚቻል

<< ወደ HELP የኖርዌይ መነሻ ገጽ ተመለስ
>> በHELP መነሻ ገጻችን ሌላ ሀገር ይምረጡ