አንድ የቅርብ የቤተሰብ አባል በኖርዌይ ውስጥ ጊዜያዊ የጋራ ጥበቃ የተሰጠው ከሆነ ለቤተሰብን ዳግም ውህደት እንዴት ማመልከት እችላለሁ?
ከዩክሬን የሸሸ ሰው የቅርብ የቤተሰብ አባል ከሆኑ እና ለጊዜያዊ የጋራ ጥበቃ ብቁ ከሆኑ ዜግነትዎ ምንም ይሁን ምን ጊዜያዊ የጋራ ጥበቃ ሊሰጥዎ ይችላል።
ከዩክሬን የሸሸ ሰው የቅርብ የቤተሰብ አባል፦
- የትዳር አጋር ሊሆኑ ይችላሉ
- አብሮ የሚኖር ሊሆኑ ይችላሉ
- ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች ሊሆኑ ይችላሉ
- ሌሎች የቤተሰብ አባላት ከየካቲት 24 ቀን 2022 በፊት ጊዜያዊ የጋራ ጥበቃ ከሚያገኘው ሰው ጋር በአንድ ቤተሰብ ውስጥ የነበሩ (የሌሎች የቤተሰብ አባላት ምሳሌዎች ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ የሆኑ ልጆች፣ አያቶች ወይም ወንድሞችና እህቶች ሊሆኑ ይችላሉ)
ከእነዚህ ምድቦች ውስጥ በአንዱም የማይመደቡ ከሆነ እና ነገር ግን በኖርዌይ ውስጥ ለቤተሰብ ዳግም ውህደት ማመልከት ከፈለጉ በመደበኛ የቤተሰብ ኢሚግሬሽን አሰራሮች ውስጥ ማለፍ አለብዎት
በኖርዌይ ውስጥ ስለቤተሰብ ዳግም ውህደት ሂደት ቪዲዮዎችን ለመመልከት ከዚህ በታች ያሉትን አገናኞች ይጫኑ።
የኖርዌይ ኢሚግሬሽን ዳይሬክቶሬት (UDI) የቤተሰብ ኢሚግሬሽን/የቤተሰብ ዳግም ውህደት ጉዳዮችን ያስተናግዳል።
ትኩረት! የቤተሰብ ዳግም ውህደት ሂደት በነጻ የሚከናወን አይደለም። ስለዚህ ጉዳይ የበለጠ እዚህ ያንብቡ።
በኖርዌይ ለሚኖረው የቤተሰብ አባል የገቢ መስፈርትም አለ። ስለዚያ የበለጠ መረጃ ለማግኘት እዚህ ማንበብ ይችላሉ።
አንድ የቅርብ የቤተሰብ አባል በኖርዌይ ውስጥ ጥገኝነት ከተሰጠው ለቤተሰብ ዳግም ውህደት እንዴት ማመልከት እችላለሁ?
የቤተሰብዎ አባል በስደተኛነት በኖርዌይ ውስጥ ጥገኝነት (ጥበቃ) የተሰጠው ከሆነ ሁለት የማመልከቻ ቀነ ገደቦችን ካሟሉ ያለ የገቢ መስፈርት ለቤተሰብ ውህደት ማመልከት ይችላሉ።
- እርስዎ፣ ከኖርዌይ ውጭ ሆነው ለቤተሰብ ውህደት የሚያመለክቱ እንደመሆንዎ፣ ማመልከቻዎን በUDI ድህረ ገጽ ላይ በኖርዌይ ውስጥ ያለው የቤተሰብዎ አባል የመኖሪያ ፍቃድ በተሰጠ በስድስት ወራት ውስጥ ማስመዝገብ አለብዎት። በተጨማሪም ማመልከቻዎን በሚያስገቡበት ጊዜ ክፍያ መክፈል ይኖርብዎታል።
- ከዚያም በሚኖሩበት አገር የሚጠየቁትን ሰነዶች ለማስረከብ የት መሄድ እንዳለብዎ ይነገርዎታል። ሰነዶቹን በግል ማስረከብ አለብዎት። የቤተሰብዎ አባል ኖርዌይ ውስጥ የመኖሪያ ፈቃድ ከተሰጠው በኋላ ሰነዶቹን በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ማስገባት አለብዎት።
ለቤተሰብ ኢሚግሬሽን ወይም ለቤተሰብ ውህደት ለማመልከት www.udi.no/skal-sokeን ይጎብኙ
ለቤተሰብ ዳግም ውህደት ሂደት የህግ እርዳታ ከየት ማግኘት እችላለሁ?
የኖርዌይ የጥገኝነት ጠያቂዎች ድርጅት (NOAS) በቤተሰብ ኢሚግሬሽን/የቤተሰብ ዳግም ውህደት ጉዳዮች ላይ ነፃ የሕግ ድጋፍ ይሰጣል።
በሌላ አገር የጠፋ የቤተሰብ አባልን ለማግኘት እርዳታ ያስፈልገኛል (የቤተሰብ ፍለጋ)
ከቤተሰብዎ አባላት ጋር ያለዎትን ግንኙነት ካጡ እና እነሱን ለማግኘት እርዳታ ከፈለጉ፣ የኖርዌይ ቀይ መስቀልን ማነጋገር ይችላሉ።
ኢሜይልን ለእነሱ መላክ ይችላሉ፦
- በኢሜይል፦ 📧 [email protected]
- በስልክ፦ በ 📞 +47 22 05 40 00 ይደውሉላቸው።
- በአካል በመገኘት የሚከተለውን አድራሻ በመጠቀም ቢሮዋቸውን ይጎብኙ፦ Hausmannsgate 7, 0186 Oslo
አገልግሎቶቻቸው ነፃና ሚስጥራዊ ነው!
UNHCR የቤተሰብ ፍለጋ አገልግሎቶችን አይሰጥም።