በ UNHCR እና በአጋሮቻችን የሚቀርቡት መረጃዎችና አገልግሎቶች በሙሉ ለጊዜያዊ ጥበቃ ተጠቃሚዎች፣ ለጥገኝነት ጠያቂዎች፣ ለስደተኞች፣ እንደ ስደተኛ ለመሆን ብቁ ላልሆኑት የሚሰጠው ጥበቃ ተጠቃሚዎችና ዜግነት ለሌላቸው ሰዎች በነጻ ይሰጣሉ።
UNHCR በዓለም ዙሪያ የጊዜያዊ ጥበቃ ተጠቃሚዎችን፣ የጥገኝነት ጠያቂዎችን፣ የስደተኞች እና ዜግነት የሌላቸው የመሆን አደጋ ተጋርጦባቸው ያሉ ሰዎችን መብት ለመጠበቅ እና የተሻለ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ለመደገፍ ይሰራል።
በኖርዌይ ውስጥ UNHCR ከዓለም አቀፍ እና ከአውሮፓውያን መስፈርቶች ጋር በሚስማማ መልኩ ተግባሮቹን እንዲያከናውኑ ብሔራዊ ባለሥልጣናትን ይደግፋል። UNHCR በኖርዌይ ውስጥ ጥገኝነት ጠያቂዎችን አይመዘግብም። በኖርዌይ ውስጥ የጥገኝነት አሰራር በኖርዌይ ፖሊስ፣ በኢሚግሬሽን ዳይሬክቶሬት እና በኢሚግሬሽን ይግባኝ ቦርድ ኃላፊነት ስር ነው።
UNHCR በኖርዌይ ውስጥ አካላዊ ቢሮ የለውም፣ ነገር ግን በስቶክሆልም (ስዊድን) የሚገኘው የ UNHCR ኖርዲክ እና ባልቲክ አገራት ውክልና ለኖርዌይ ኃላፊነት አለበት።
እኛን ያነጋግሩን
በዚህ ‘HELP (እርዳታ)’ ድህረ ገጽ ላይ የሚፈልጉትን መረጃ ካላገኙ እባክዎ በስልክ ወይም በኢሜይል ለማነጋገር ነጻነት ይሰማዎት፦
ስልክ፦ 📞 +46 10 10 12 800 (ሰኞ – አርብ፣ ከ10.00 እስከ 12.00 እና ስቶክሆልም ሰዓት አቆጣጠር)
ኢሜይል፦ 📧 [email protected]
እንግሊዝኛ ወይም ስዊድንኛ የማይናገሩ ከሆነ
ምንም እንኳን እኛ በእንግሊዝኛ ወይም በስዊድንኛ ብቻ ጥሪዎችን መመለስ የምንችል ቢሆንም ሁኔታዎን በመግለጽ በሚመርጡት ቋንቋ ኢሜይል መላክ የሚችሉ ሲሆን እኛ መልስ እንሰጥዎታለን። ምላሻችን በአብዛኛዎቹ ጊዜ በእንግሊዘኛ ይሆናል፣ ነገር ግን ለመረዳት ከተቸገሩ Google Translateን እንዲጠቀሙ ወይም ግልጽ እንድናረግልዎ የሚጠይቅ ኢሜይል እንዲልኩልን እናበረታታዎታለን።