ለቤተሰብ ዳግም ውህደት ማመልከት

በስዊድን ውስጥ ጥገኝነት የተሰጠዎት ከሆነ፣ እና ከቤተሰብዎ ተለያይተው ከሆነ፣ ቤተሰብዎ በተወሰኑ ሁኔታዎች ስር በስዊድን ውስጥ ከእርስዎ ጋር እንዲቀላቀል ለቤተሰብ ዳግም ውህደት ማመልከት ይችላሉ።

ስለቤተሰብ ውህደት ተጨማሪ መረጃ ማግኘት እና ማመልከት የሚችሉት በስዊድን የስደተኞች ኤጄንሲ ድህረ-ገጽ ላይ ሲሆን፣ ድህረ-ገጹ በበርካታ ቋንቋዎች ይገኛል።

የገቢ መስፈርቶች አሉ?

በስዊድን ውስጥ ከቤተሰብዎ ጋር ለመገናኘት ከፈለጉ፣ ለቤተሰብዎ የገንዘብ ድጋፍ እና የተወሰነ ደረጃ ያለው መኖሪያ እንዲኖርዎት የሚጠይቁ መስፈርቶች ሊኖሩ ይችላሉ። ይህ ደግሞ “የጥገና ግዴታ” ይባላል።

በስዊድን የስደተኛነት ጥበቃ ከተሰጠዎት እና ከቤተሰብዎ ጋር ዳግም ለመገናኘት ከፈለጉ ውሳኔዎን ከተቀበሉበት ቀን ጀምሮ ለ3 ወራት ያህል ከጥገና ግዴታ ነፃ ይሆናሉ። ዳግም የተሰደዱ ስደተኛ ከሆኑ ተመሳሳይ ነገር እንደሚከሰት እባክዎ ልብ ይበሉ።

በስዊድን ውስጥ እንደ ስደተኛ ለመሆን ብቁ ላልሆኑት የሚሰጠው ጥበቃ ከተደረገልዎት እና ከቤተሰብዎ ጋር ዳግም ለመገናኘት ከፈለጉ፣ የጥገና ግዴታ ተፈጻሚ ይሆናል።

ከማን ጋር ዳግም መገናኘት እችላለሁ?

የትዳር አጋርዎ፣ የተመዘገበ ወይም አብሮ የሚኖር አጋርዎ እንዲሁም፣ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች አብረውዎት ስዊድን የመኖር እድል አላቸው። ከቤተሰብዎ ጋር ዳግም የመገናኘት ማመልከቻዎ ተቀባይነት ካገኘ፣ የቤተሰብዎ አባላት ወደ ስዊድን እንዲመጡ ጉዞውን ማደራጀትና ወጪውን መክፈል ይኖርብዎታል። እንደ Miles4Migrants ያሉ፣ አንዳንድ ድርጅቶች ወይም ፕሮጀክቶች ሊረዱ ይችላሉ። ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት Miles4Migrants ድህረ-ገጽን ይጎብኙ።

በልዩ ሁኔታዎች ውስጥ፣ በትውልድ ሀገርዎ ከእርስዎ ጋር አብረው የኖሩ እና በእርስዎ ላይ ሙሉ በሙሉ ጥገኛ የሆኑ ሌሎች የቤተሰብዎ አባላት በስዊድን ከእርስዎ ጋር ሊኖሩ ይችላሉ።

ቤተሰብን ዳግም የማግኘት ማመልከቻ ውድቅ ከተደረገ ይግባኝ ማለት እችላለሁ?

የስዊድን የስደተኞች ኤጄንሲ ለቤተሰብዎ ዳግም መገናኘት ያቀረቡትን ጥያቄ ውድቅ ካደረገ፣ ለስደተኞች ጉዳይ ፍርድ ቤት አቤቱታ የማቅረብ መብት አለዎት።

ይግባኙን ማቅረብ ያለብዎት ከስዊድን የስደተኞች ኤጄንሲ የቤተሰብ ዳግመኛ መገናኘት ማመልከቻዎን በተመለከተ ውሳኔ የተሰጠበትን ደብዳቤ ከተቀበሉ በኋላ ባሉት 3 ሳምንታት ውስጥ መሆኑን ልብ ይበሉ። በዚህ ደብዳቤ ላይ በውሳኔው ላይ ይግባኝ ለማለት ምን ያህል ጊዜ እንዳለዎት ይገልጻል።

ውድቅ የተደረገ ውሳኔን እንዴት ይግባኝ ማለት እንደሚቻል ተጨማሪ መረጃ በስዊድን የስደተኞች ኤጄንሲ ድህረ-ገጽ ላይ በእንግሊዝኛ እና በስዊድንኛ ያንብቡ።

ለቤተሰብ ዳግም መገናኛ ሂደት እርዳታ ማግኘት የምችለው ከየት ነው?

በቤተሰብ ውህደት ላይ የሕግ ምክር ለማግኘት፣ ለጉዳያችዎ ነፃ የህግ ምክር ሊያቀርቡልዎ የሚችሉትን የስዊድን የስደተኞች የሕግ ማዕከል ወይም የስዊድን ቀይ መስቀል የተባሉ አጋሮቻችንን እንዲያነጋግሩ እንመክራለን።

በስዊድን፣ ዩኤንኤችሲአር የአገሪቱ ባለሥልጣናት ከዓለም አቀፍና ከአውሮፓ መስፈርቶች ጋር በሚስማማ መልኩ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ይደግፋል። ዩኤንኤችሲአር በስዊድን የቤተሰብ ዳግም ማገናኛ አሰራር ውስጥ አይሳተፍም። በስዊድን ውስጥ ያለው አሰራር የስዊድን የስደተኞች ኤጄንሲ ኃላፊነት ነው።


ተዛማጅ መረጃ