ስለ UNHCR በስዊድን

በ UNHCR እና በአጋሮቻችን የሚቀርቡት መረጃዎችና አገልግሎቶች በሙሉ ለጊዜያዊ ጥበቃ ተጠቃሚዎች፣ ለጥገኝነት ጠያቂዎች፣ ለስደተኞች፣ እንደ ስደተኛ ለመሆን ብቁ ላልሆኑት የሚሰጠው ጥበቃ ተጠቃሚዎችና ዜግነት ለሌላቸው ሰዎች በነጻ ይሰጣሉ።

የተመድ የስደተኞች ኤጀንሲ ዩኤንኤችሲአር በግጭት እና በስደት ምክንያት ቤታቸውን ጥለው ለመሰደድ የተገደዱ ሰዎችን ይጠብቃል። ህይወትን እናድናለን፣ መብቶችን እንጠብቃለን እንዲሁም የተሻለ የወደፊት ሕይወት ለመገንባት እንረዳለን።

በስዊድን ውስጥ፣ ዩኤንኤችሲአር ከዓለም አቀፍ እና ከአውሮፓ ደረጃዎች ጋር በሚስማማ መልኩ ግዴታዎቻቸውን እንዲፈጽሙ ብሔራዊ ባለሥልጣናትን ይደግፋል ። ዩኤንኤችሲአር የስዊድን የጥገኝነት አሰራር አካል አይደለም። በስዊድን ውስጥ የጥገኝነት አሰራር የስዊድን የስደተኞች ኤጄንሲ ኃላፊነት ነው።

በስዊድን የሚገኘው የዩኤንኤችሲአር የኖርዲክና የባልቲክ አገሮች የዩኤንኤችሲአር ውክልና አካል ሲሆን መቀመጫውም ስቶክሆልም (ስዊድን) ነው።

ዩኤንኤችሲአርን ያነጋግሩ

በዚህ  ‘እርዳታ’ ድህረ-ገጽ ላይ የሚፈልጉትን መረጃ ካላገኙ እባክዎ በስልክ ወይም በኢሜይል ያነጋግሩን፦

ስልክ፦  📞 +46 10 10 12 800 (ከሰኞ እስከ አርብ በስቶክሆልም ሰዓት ከ10፡00 እስከ 12፡00)

ኢሜይል፦  📧 [email protected]

እንግሊዝኛ ወይም ስዊድንኛ የማይናገሩ ከሆነ

ምንም እንኳን እኛ በእንግሊዝኛ ወይም በስዊድንኛ ብቻ ጥሪዎችን መመለስ የምንችል ቢሆንም ሁኔታዎን በማብራራት በሚመርጡት ቋንቋ ኢሜይል መላክ ይችላሉ እና እኛ መልስ እንሰጥዎታለን። መልሳችን በአብዛኛው ጊዜ በእንግሊዝኛ ይሆናል፣ ነገር ግን ለመረዳት ችግር ካጋጠምዎት Google Translate እንዲጠቀሙ ወይም ለማብራራት ሌላ ኢሜይል እንዲልኩልን እንመክራለን።


ተዛማጅ መረጃ