ወደ ኖርዌይ ለመግባት ከእንግዲህ ከኮቪድ-19 ጋር የተያያዙ ገደቦች የሉም። ጥገኝነት ጠያቂዎች ከዚህ ቀደም ለኮቪድ-19 ያልተመረመሩ፣ ያላገገሙ ወይም ያልተከተቡ ቢሆኑም እንኳ ወደ ኖርዌይ መግባት ይችላሉ። ጠቃሚ መረጃዎችን ለማግኘት እና ለክትባት ቀጠሮ ለመያዝ ከዚህ በታች ያሉትን ሊንኮች/አገናኞች ይጠቀሙ፦
- ስለ ኮቪድ-19፣ ለይቶ ማቆያ፣ ክትባቶች እና ስለ ኮቪድ-19 የምስክር ወረቀቶች መረጃ ለማግኘት እዚህ ይጫኑ
- ስለ ኮቪድ-19 አጠቃላይ መረጃን፣ የመረጃ ወረቀቶችን እና ቪዲዮዎችን በበርካታ ቋንቋዎች ለማግኘት እዚህ ይጫኑ
- ለኮቪድ-19 ክትባት ቀጠሮ ለመያዝ እዚህ ይጫኑ።.
- ስለ ኮቪድ-19 ጥያቄዎች ካለዎት የሄልሴ ኖርዌ (Helse Norge) መረጃ መስመርን በ 📞 815 55 015 ላይ ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 8፡00 እስከ ከሰዓቱ 15፡30 ድረስ ይደውሉ።