በኖርዌይ ውስጥ ጥበቃ ለሚፈልጉ ከዩክሬን ለሚሸሹ ሰዎች መረጃ

በኖርዌይ ውስጥ ያሉ ከዩክሬን የመጡ ስደተኛ ከሆኑ፣ እባክዎን አስፈላጊ መረጃዎችን በእንግሊዝኛ፣ በኖርዌይኛ፣ በዩክሬንኛ እና በሩሲያኛ የያዘውን የኖርዌይ መንግስት ኢሚግሬሽን ዳይሬክቶሬት ድህረ-ገጽ ይጎብኙ። እንዲሁም ወደ የኖርዌይ ኢሚግሬሽን ዳይሬክቶሬት (Utlendingsdirektoratet – UDI) በስልክ ቁጥር 📞 +47 23 35 15 00 (ሰኞ/አርብ ከጠዋቱ 8 ሰዓት እስከ ከሰዓት 3 ሰዓት) መደወል ይችላሉ።

ከዩክሬን በመሸሽ በፖላንድ፣ በሃንጋሪ፣ በጣሊያን፣ በስሎቫኪያ፣ በሩማኒያ፣ በቡልጋሪያ ውስጥ ከሆኑ፣ እባክዎን ስለ መብቶች እና አገልግሎቶች እንዲሁም እርዳታ የት እንደሚያገኙ መረጃን በዲጂታል ሰማያዊ ነጥብ (Digital Blue Dot) ላይ ያግኙ። ጣቢያው በዩክሬንኛ እና በሩሲያኛም ይገኛል።  

በኖርዌይ ውስጥ ለጊዜያዊ የጋራ ጥበቃ እንዴት ማመልከት እንደሚቻል

ከዩክሬን የሸሹ ሰዎች ለአንድ ዓመት ጊዜያዊ የጋራ ጥበቃ ሊደረግላቸው ይችላል። የጋራ ጥበቃ ማለት የኖርዌይ ኢሚግሬሽን ዳይሬክቶሬት (UDI) የጥበቃ አስፈላጊነትን በግለሰቦች ደረጃ አይገመግምም ነገር ግን በዩክሬን ጦርነት ለሚሸሹ ዩክሬናውያን እና ለቤተሰቦቻቸው አባላት የጋራ ጥበቃ ይሰጣል። ይህም ከጦርነቱ የሚሸሹ ዩክሬናውያን የሚያስፈልጋቸውን እርዳታ በፍጥነት እንዲያገኙ ያደርጋል።

የኖርዌይ ኢሚግሬሽን ዳይሬክቶሬት (UDI) ከዩክሬን የተፈናቀሉ ሰዎች ጊዜያዊ ጥበቃ ለማግኘት የሚያስገቡትን ማመልከቻዎች የማስኬድ ኃላፊነት አለበት።

ጊዜያዊ የጋራ ጥበቃ ሊሰጥዎ የሚችለው እርስዎ፡-

  • የዩክሬን ዜጋ ከሆኑ እና ከየካቲት 24 ቀን 2022 በፊት በዩክሬን ውስጥ የኖሩ (ከ የካቲት 24 ቀን ትንሽ ቀደም ብሎ ከዩክሬን ለለቀቁ ሰዎች የተወሰነ ተለዋጭነት አለ)
  • ከ የካቲት 24 ቀን 2022 በፊት እስከ 90 ቀናት ድረስ ከዩክሬን ውጭ በበዓል ወይም በእረፍት ላይ የነበሩ ወይም ከዩክሬን ውጭ የጎበኙ የዩክሬን ዜጋ ከሆኑ
  • የዩክሬን ዜጋ ከሆኑ እና ከ የካቲት 24 ቀን 2022 በፊት በኖርዌይ ውስጥ ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ኖሯቹ፣ እና ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ጊዜው ካለፈበት ወይም ለጥበቃ ካመለከቱ በኋላ ከሁለት ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ ጊዜው ካበቃ
  • በዩክሬን ውስጥ ከየካቲት 24 ቀን 2022 በፊት ጥበቃ የተሰጥዎት ከሆነ፣ ለምሳሌ፣ እውቅና እንደተሰጠው ስደተኛ
  • ዜግነትዎ ምንም ይሁን ምን ለጊዜያዊ የጋራ ጥበቃ ብቁ የሆነ ሰው የቅርብ የቤተሰብ አባል* ከሆኑ

*የቅርብ የቤተሰብ አባል የትዳር አጋር፣ አብሮ የሚኖር ሰው፣ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች እና ሌሎች የቤተሰብ አባላት ከየካቲት 24 ቀን 2022 በፊት ጊዜያዊ የጋራ ጥበቃን ከሚያገኝ ሰው ጋር በአንድ ቤተሰብ ውስጥ የነበሩ ሊሆኑ ይችላሉ። ሌሎች የቤተሰብ አባላትም ምሳሌዎች ከ18 ዓመት በላይ የሆኑ ልጆች፣ አያቶች ወይም ወንድሞችና እህቶች ሊሆኑ ይችላሉ።

ከላይ በተጠቀሱት ምድቦች ውስጥ የማይመደቡ ከሆነ አሁንም ቢሆን ጥገኝነት መጠየቅ የሚችሉ ሲሆን ማመልከቻዎ የሚመዘነው እና የሚገመገመው በተናጠል ነው።

ለጊዜያዊ የጋራ ጥበቃ ለማመልከት፣ ፖሊስን በመጠየቅ ለምዝገባ ቀጠሮ መያዝ ይኖርብዎታል። ለእያንዳንዱ የፖሊስ ወረዳ ወይም ድስትሪክት የእውቂያ ዝርዝሮችን በዚህ ድህረ-ገጽ ላይ ያገኛሉ።

ጊዜያዊ ጥበቃ ለማግኘት በኖርዌይ ፖሊስ ሲመዘገቡ ምን ይከሰታል

  • ፖሊስ መረጃዎን በኤሌክትሮኒክ መንገድ ይመዘግባል እንዲሁም የጣትዎን አሻራ ይወስዳል። ፓስፖርት ወይም ሌሎች የመታወቂያ ሰነዶች ካልዎት እነዚያን ለፖሊስ ማሳየት አለብዎት።
  • ፖሊስ ፓስፖርትዎን እና የመታወቂያ ሰነዶችዎን በመቃኘት መልሶ ይሰጥዎታል።
  • ለጥገኝነት ጠያቂዎች የሚሰጥ ካርድ ከፖሊስ ያገኛሉ።
የጥገኝነት ጠያቂ መታወቂያ ካርድ ናሙና  – የፊት ገጽ
የጥገኝነት ጠያቂ መታወቂያ ካርድ ናሙና  – የኋላ ገጽ

➡️በኖርዌይ ውስጥ በዚህ ካርድ መጠቀም ስለሚችሉት እና ስለማይችሉት ነገሮች መረጃ ለማግኘት የኖርዌይ መንግስት የUDI ድህረ-ገጽን ይጎብኙ።

  • ከጥገኝነት ጠያቂ ካርድዎ ጋር፣ ከኖርዌይ ፖሊስ የዲ ቁጥር ያገኛሉ። የD ቁጥር በኖርዌይ ውስጥ የመታወቂያ ቁጥር በሚፈልጉበት ጊዜ ከኖርዌይ ግብር አስተዳደር የሚቀበሉት ጊዜያዊ የመታወቂያ ቁጥር ነው። የD  ቁጥር በጥገኝነት ጠያቂ ካርድ በታችኛው ቀኝ ጥግ ላይ ይታያል።

➡️የኖርዌይ መንግስት የUDI ድህረ ገጽን በመጎብኘት የD ቁጥር ምን እንደሆነ እና ለምን እንደሚያስፈልግዎ ተጨማሪ መረጃ ያግኙ።

በኖርዌይ ፖሊስ ለጊዜያዊ የጋራ ጥበቃ ማመልከቻውን ካስመዘገቡ በኋላ ምን ይከሰታል?

  • በተጨማሪም የሳንባ ነቀርሳ (ቲቢ) ምርመራ ማድረግ ይኖርብዎታል።
  • በድንገተኛ ማረፊያ ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ፣ የሳንባ ነቀርሳ ምርመራ የሚደረግበት ቦታና ጊዜ ይነገርዎታል።
  • በግል መኖሪያ ቤት ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ፣ የሳንባ ነቀርሳ ምርመራ እንዴት ማድረግ እንደሚቻል መረጃ ለማግኘት የማዘጋጃ ቤት የጤና አገልግሎትን ማነጋገር ይችላሉ።
  • የመቆያ ቦታ የሚፈልጉ ከሆነ፣ ማመልከቻዎን በሚያስገቡበት ጊዜ ለፖሊስ ማሳወቅ ይችላሉ። ፖሊስ የኖርዌይ ኢሚግሬሽን ዳይሬክቶሬትን (UDI) ያነጋግራል። UDI በድንገተኛ ማረፊያ ውስጥ ቦታ ያገኝልዎታል።
  • የእርስዎን D  ቁጥር ሲሰጥዎት፣ የሚያስፈልጉዎትን የጤና አገልግሎቶች ማግኘት ይችላሉ።
  • በብሔራዊ የመድረሻ ማዕከል (National Arrival Centre) ከተመዘገቡ፣ አሰራሩ ከላይ ከተገለጸው ጋር ተመሳሳይ ነው

በደቡብ ምስራቅ ኖርዌይ ራዴ ውስጥ በሚገኘው ብሔራዊ የመድረሻ ማዕከል ሲደርሱ ምን እንደሚከሰት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በዩክሬንኛበሩሲያኛበእንግሊዝኛ እና በኖርዌይኛ መረጃ ለማግኘት እዚህ ይጫኑ።

ጊዜያዊ ጥበቃ ለማግኘት በኖርዌይ ፖሊስ በኩል የሚደረገውን የማመልከቻ ሂደቱን ካጠናቀቁ በኋላ ምን ይከሰታል (ሁሉም አመልካቾች)

የምዝገባ ሂደቱን ካጠናቀቁ በኋላ የኖርዌይ ፖሊስ ማመልከቻዎን ወደ የኖርዌይ ኢሚግሬሽን ዳይሬክቶሬት (UDI) ይልካል።

UDI እርስዎ ፈጣን መልስ ማግኘት እንዲችሉ ማመልከቻዎችን በተቻለ ፍጥነት ለማካሄድ ይሞክራል። አንዳንዶቹ ጉዳዮች በራስ-ሰር በሮቦት የሚከናወኑ ሲሆን፣ ሌሎቹ ጉዳዮች ደግሞ በጉዳይ መኮንኖች ይከናወናሉ። ይህ UDI በየቀኑ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ጉዳዮች እንዲያጠናቅቅ ይረዳል።

አንዳንድ ጊዜ UDI እርስዎን ለንግግር ወይም ለቃለ መጠይቅ መጥራት እንዲችሉ ተጨማሪ መረጃ ሊፈልግ ይችላል። ይህ የሚያስፈልግ ከሆነ እንዲያውቁት ይደረጋል።

UDI ማመልከቻዎን በሚያስኬድበት ጊዜ መስራት ወይም ለሥራ ማመልከት አይችሉም። በኖርዌይ ውስጥ ጊዜያዊ የጋራ ጥበቃ ከተሰጥዎት በኋላ ብቻ ነው እንዲሰሩ የሚፈቀድልዎት።

ማመልከቻዎ ምላሽ እስኪያገኝ ድረስ የትኞቹን አገልግሎቶች ማግኘት ይችላሉ?

  • በድንገተኛ አደጋ ጊዜ፣ ለፖሊስ በ 📞 112 ላይ ይደውሉ። አስቸኳይ ጉዳይ ካልሆነ በ 📞 02800 መደወል ይችላሉ።
  • የሕክምና ድንገተኛ ሁኔታ ሲያጋጥም፣ በአቅራቢያው የሚገኘውን የድንገተኛ ክፍል ለማነጋገር ወደ 📞 +47 116 117 መደወልም ይችላሉ።
  • የፌስቡክ መለያ ካለዎት በሦስት ቋንቋዎች የሚገኙትን የዩክሬን ስደተኞችን የፌስቡክ ገጾች መመልከት ይችላሉ፦ ኖርዌይኛ፣ ዩክሬንኛ እና ሩሲያኛ።
  • በኖርዌይ ውስጥ ለጊዜያዊ የጋራ ጥበቃ ካመለከቱ እና የኖርዌይ መታወቂያ ቁጥር ከተሰጥዎት የኖርዌይ የህዝብ ባለሥልጣናት ዲጂታል አገልግሎቶችን ለመድረስ የኤሌክትሮኒክ መታወቂያ ማዘዝ ይችላሉ፣ ለምሳሌ፦ የጤና እና ደህንነት አገልግሎቶች፣ የገንዘብ ድጋፍ፣ ትምህርት መጀመር እና መከታተል፣ ዲጂታል የመልዕክት ሳጥን መዳረሻ እና ሌሎችንም መድረስ። ስለ ኤሌክትሮኒክ መታወቂያዎች እና እንዴት በ norge.no ላይ ማዘዝ እንደሚችሉ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እዚህ ይጫኑ
  • ኖርዌይ ውስጥ ለጊዜያዊ የጋራ ጥበቃ ማመልከቻዎ ምላሽ እስኪሰጥ ድረስ፣ ጥገኝነት በሚሰጥዎ የጥገኝነት መቀበያ ማዕከል ውስጥ መቆየት ይችላሉ። ይህ ቀላልና ጊዜያዊ ማረፊያ ነው። በጥገኝነት መቀበያ ማዕከል ውስጥ ሲኖሩ ምን እንደሚጠብቁ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እዚህ ይጫኑ።
  • ማመልከቻዎ ምላሽ እስኪያገኝ ድረስ ልጆች በኖርዌይ ውስጥ ትምህርት ቤት የመግባት መብት አላቸው። ይህ የሚሰራው ዕድሜያቸው ከ6 – 16 ዓመት ለሆኑ ልጆች ነው።
  • በኖርዌይ ውስጥ እንደማንኛውም ሰው ተመሳሳይ የጤና እንክብካቤ የማግኘት መብት አለዎት።

ማመልከቻዎ ተቀባይነት ካገኘ እና ከዩክሬን ለሸሹ ሰዎች ጊዜያዊ የጋራ ጥበቃ መስፈርቶችን ካሟሉ ምን ይሆናል

ስለተቀበሉት የመኖሪያ ፈቃድ መረጃ የያዘ ውሳኔ ደብዳቤ በፖስታ ይደርስዎታል። እንዲሁም መብቶችዎን እና ግዴታዎችዎን የሚያብራራ በዩክሬንኛ የተጻፈ ደብዳቤም ይደርስዎታል።

በደብዳቤው ውስጥ፣ መብቶችዎን እና ግዴታዎችዎን የሚያብራራ በእርስዎ ቋንቋ ወደሚገኝ ቪዲዮ የሚያገናኝ QR ኮድ ይኖራል። ቪዲዮውን መመልከቱ በጣም አስፈላጊ ነው። ቪዲዮውን ለመመልከት፣ QR ኮዱን ለመቃኘት ስልክዎን መጠቀም ወይም በሚደርስዎት ደብዳቤ ላይ ያለውን አገናኝ መጠቀም ይኖርብዎታል።

በጥገኝነት መቀበያ ማዕከል ወይም በድንገተኛ ጊዜ ማረፊያ ውስጥ ካልኖሩ፣ እባክዎን የዘመነ አድራሻዎን ለፖሊስ መስጠትዎን ያረጋግጡ።

በግል መኖሪያ ቤት ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ፣ UDI የሚልክልዎትን ደብዳቤዎች ለመቀበል ስምዎ በፖስታ ሳጥን ላይ መሆን አለበት።

➡️ጊዜያዊ የጋራ ጥበቃ ሲያገኙ ስለመብቶችዎ እና ግዴታዎችዎ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ።

የመኖሪያ ፈቃድ ከተሰጥዎት በኋላ፣ ኢሜይል ይደርስዎታል። የመኖሪያ ካርድም ይደርስዎታል። ለመጀመሪያ ጊዜ ማመልከቻዎን ሲያቀርቡ ከተቀበሉት የጥገኝነት ጠያቂ ካርድ የመኖሪያ ካርድ የተለየ ነው። የመኖሪያ ካርድ ለማግኘት ፎቶና የጣት አሻራዎችን ለመውሰድ ወደ ፖሊስ ጣቢያ መሄድ ሊያስፈልግዎት ይችላል። ከዚህ በፊት ፎቶግራፍዎ እና የጣትዎ አሻራዎች ከተወሰዱ፣ እንደገና እንዲወሰድ ለማድረግ ወደ ፖሊስ ጣቢያ መሄድ ላያስፈልግዎ ይችላል። ለፖሊስ ሪፖርት ማድረግ ካስፈለገዎት ይነገርዎታል። የመኖሪያ ፈቃድ ካርድዎ ከደረስዎት በኋላ ብሔራዊ የመታወቂያ ቁጥር እንደተሰጥዎት የሚገልጽ ደብዳቤ ይደርስዎታል።

➡️ስለ ኖርዌይ የመኖሪያ ካርዶች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እዚህ ይጫኑ።.

ለጊዜያዊ የጋራ ጥበቃ የሚሰጥ የመኖሪያ ፈቃድ መጀመሪያ ላይ ለአንድ ዓመት የሚሰራ ሲሆን፣ ከዚያ በኋላ በየጊዜው ለአንድ ዓመት ሊታደስ ይችላል።

በኖርዌይ ውስጥ እንደ የጊዜያዊ ጥበቃ ባለቤት ያሉዎት መብቶች እና ግዴታዎች ምንድን ናቸው?

➡️ጊዜያዊ የጋራ ጥበቃ ከተሰጠዎት በኋላ ስለ መብቶችዎ እና ግዴታዎችዎ መረጃ ለማግኘት እዚህ ይጫኑ

  • የጋራ ጥበቃ ፈቃድዎ የሚሰጠው በአንድ ጊዜ ለአንድ ዓመት ነው።
  • በሕዝብ የጤና እንክብካቤ አገልግሎቶች በኩል የጤና እንክብካቤ የማግኘት መብት አለዎት
  • በኖርዌይ ውስጥ የመሥራት መብት አለዎት
  • ልጆችዎ ትምህርት ቤት እና መዋለ ህፃናት / ቅድመ-ትምህርት ቤት የመከታተል መብት አላቸው
  • የኖርዌይ ባለሥልጣናት የመኖሪያ ቦታ (ሰፈራ) ሊሰጥዎት ይችላሉ። ይህ ማለት በከተማው ውስጥ ለመኖር የሚያስችል ቦታ ለማግኘት እርዳታ ያገኛሉ ማለት ነው። ስለ ሰፈራ ተጨማሪ መረጃ እዚህ ያንብቡ።
  • እድሜዎ ከ18 እስከ 55 ዓመት ከሆነ የመግቢያ ፕሮግራም የመቀላቀል መብት አለዎት።
  • በጊዜያዊ የጋራ ጥበቃ ደንቦች ያልተሸፈኑ የቤተሰብዎ አባላት በተለመዱት ደንቦች መሠረት ወደ ኖርዌይ በቤተሰብ ለመሰደድ ማመልከት ይችላሉ።
  • በሂደቱ በሙሉ ሐቀኛ እና እውነተኛ መረጃ መስጠት አስፈላጊ ነው። ትክክለኛ ያልሆነ መረጃ ከሰጡ ወይም ለባለሥልጣናት አስፈላጊ መረጃን ሳይጠቅሱ ከቀሩ፣ ፍቃድዎ ሊሰረዝ ይችላል።
  • የጉዞ ሰነድ ይዘው ወደ ኖርዌይ የመግባትና ከኖርዌይ የመውጣት መብት አለዎት። ይህ የራስዎ ብሔራዊ ፓስፖርት ወይም በኖርዌይ ባለሥልጣናት የተሰጠ የጉዞ ሰነድ ሊሆን ይችላል። ወደ ዩክሬን ለመጓዝ ተፈቅዶልዎታል።

ለጊዜያዊ ጥበቃ ያስገቡት ማመልከቻዎ ውድቅ ከተደረገ ምን ይከሰታል?

ማመልከቻዎ ወዲያውኑ በመደበኛ የጥገኝነት አሰራር መሠረት እንደ የግለሰብ የጥገኝነት ጉዳይ እንዲሰናዳ ይተላለፋል።

➡️በኖርዌይ ውስጥ ስላለ መደበኛ የጥገኝነት አሰራር ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እዚህ ይጫኑ።


<< ወደ HELP የኖርዌይ መነሻ ገጽ ተመለስ
>> በHELP መነሻ ገጻችን ሌላ ሀገር ይምረጡ