ጥገኝነት ሲያመለክቱ ምን ይከሰታል

ደረጃ 1 – መድረሻ እና ምዝገባ

  • ኖርዌይ ሲደርሱ ለጥገኝነት ማመልከት ከፈለጉ ፖሊስን ማነጋገር ያስፈልግዎታል።
  • ጥበቃ ለማግኘት በፖሊስ በኩል የሚያመለክቱ ሁሉ ወደ የብሔራዊ ፖሊስ ኢሚግሬሽን አገልግሎት (NPIS) ይላካሉ። ይህ የሚከናወነው በ National Arrival Centre at Råde (ኦስሎ  በራድ) በሚገኘው ብሔራዊ የመድረሻ ማዕከል (National Arrival Centre) ውስጥ ነው። NPIS የጥገኝነት ማመልከቻዎን ይመዘግባል።
  • ወደ ብሔራዊ የመድረሻ ማዕከል ከደረሱ በኋላ ምግብና መጠጥ እንዲሁም ለመኖርና ለመተኛት የሚያስችል አስተማማኝ ቦታ ይሰጥዎታል።
  • ከ NPIS ጋር ተነጋግረው እንደ ጥገኝነት ጠያቂ ይመዘገባሉ። ፎቶዎና የጣት አሻራዎችዎ ይወሰዳል። የእርስዎን ፓስፖርት ወይም ሌላ የማንነት ሰነዶች ካልዎት ለፖሊስ ማሳየት ይኖርብዎታል።
  • የሚያስፈልግዎ ከሆነ አስተርጓሚ ይኖራል።
  • ጥገኝነት ለማግኘት እንዳመለከቱ የሚያሳይ ካርድ ይደርስዎታል።
  • ሐኪም ወይም ነርስ የሳንባ ነቀርሳ ምርመራ ያደርጉልዎታል።
  • ለጥገኝነት ጠያቂዎች ገለልተኛ ድርጅት ማነጋገር ይችላሉ። Caritas ይባላሉ። Caritas ጥገኝነት ጠያቂ መሆን ምን ማለት እንደሆነ መረጃ ይሰጥዎታል። የእውቂያ መረጃ እዚህ ይገኛል።
  • ከላይ የተጠቀሱትን ደረጃዎች በሙሉ ለማጠናቀቅ እስከ 21 ቀናት ሊወስድ ይችላል። በዚህ ጊዜ፣ በብሔራዊ የመድረሻ ማዕከል ውስጥ ይቆያሉ።
  • ይህ የምዝገባ ሂደት ከተጠናቀቀ በኋላ የኖርዌይ ኢሚግሬሽን ዳይሬክቶሬት (UDI) የጥገኝነት ጥያቄዎን በሚያስኬድበት ጊዜ ወደ ሌላ የጥገኝነት መቀበያ ማዕከል ይዛወራሉ።

ደረጃ 2 – ቃለ መጠይቅ

  • በጥገኝነት መቀበያ ማዕከል ውስጥ በሚሆኑበት ጊዜ፣ የጥገኝነት መጠየቂያ ቃለ መጠይቅዎ መቼ እንደሚደረግ እስኪነገርዎ ድረስ መጠበቅ አለብዎት።
  • በኖርዌይ የኢሚግሬሽን ዳይሬክቶሬት (UDI) መኮንን ቃለ መጠይቅ ይደረጋሉ።
  • የጥገኝነት መጠየቂያ ቃለ መጠይቁ እርስዎ ለምን ከሀገርዎ እንደወጡ እና ቢመለሱ ምን ሊከሰት ይችላል ብለው የሚያስቡትን ሁኔታ ለማብራራት እድል ይሰጥዎታል። ቃለ መጠይቁ ሚስጥራዊ ነው።
  • በጥገኝነት ቃለ መጠይቁ ወቅት የእርስዎን ቋንቋ የሚናገር አስተርጓሚ ይኖራል።
  • በሀገርዎ ውስጥ ለምን ደህንነቱ የተጠበቀ እንዳልሆነ ለUDI መንገር አለብዎት።
  • የሚናገሩት ነገር ሁሉ እስከሚያውቁት ድረስ እውነት እና ትክክለኛ መሆን አለበት።
  • የጥገኝነት ቃለ መጠይቁ ብዙ ሰዓታት ሊወስድ ይችላል፣ ነገር ግን እረፍት የመውሰድ እና ምግብ እና መጠጥ የማግኘት መብት አለዎት።
  • ከጥገኝነት ቃለ መጠይቅዎ በኋላ፣ ስለ ጥገኝነት ጉዳይዎ መልስ ለማግኘት መጠበቅ አለብዎት። ረጅም ጊዜ መጠበቅ ሊኖርብዎት ይችላል። UDI በአሁኑ ወቅት የጥገኝነት ጉዳዮችን በተመለከተ የሚሰጡ ውሳኔዎች ምን ያህል ጊዜ ሊወስዱ እንደሚችሉ ትክክለኛ የጊዜ ሰሌዳዎችን ማቅረብ አልቻለም።

< ተመለስ፡ በኖርዌይ ውስጥ ጥገኝነት ለማግኘት እንዴት ማመልከት እንደሚቻል

<< ወደ HELP የኖርዌይ መነሻ ገጽ ተመለስ
>> በHELP መነሻ ገጻችን ሌላ ሀገር ይምረጡ