ዕድሜዎ ከ18 ዓመት በታች ሆኖ ወደ ኖርዌይ የገቡና ለጥገኝነት የሚያመልክቱ ልጅ ከሆኑ፣ እርስዎ ብቻዎን የመጡ ለአካለ መጠን ያልደረሱ ጥገኝነት ጠያቂ ነዎት። የጥገኝነት ሂደቱ ከአዋቂዎች ሂደት ጋር ተመሳሳይ ነው ማለት ይቻላል። ይሁን እንጂ፣ ልጅ እንደመሆንዎ መጠን ተጨማሪ መብቶች አሉዎት፦
- በኖርዌይ ውስጥ ተወካይ የማግኘት መብት አለዎት። ተወካይ ማለት ብቻዎን ስለሆኑ እርስዎን ወክሎ የሚሰራ አዋቂ ሰው ነው። ተወካዩ በኖርዌይ ውስጥ የእርስዎን መብቶች ህጋዊም ሆነ የገንዘብ ድጋፍ ይከታተላል።
- እንዲሁም ጠበቃ ይመደብልዎታል
- የኖርዌይ ኢሚግሬሽን ዳይሬክቶሬት (UDI) እድሜዎ ከ18 ዓመት በታች መሆንዎን የሚጠራጠር ከሆነ የዕድሜ ምርመራ ይደረግልዎታል። የዕድሜ ምርመራው በሁለት ክፍሎች የተዋቀረ ነው፦ የእጅዎ እና የጥርስዎ ኤክስሬይ ወይም ራጅ። አንድ ሐኪም እነዚህን የኤክስሬዮች ወይም ራጆች ተመልክቶ ዕድሜዎን ይገመግማል
- የዕድሜ ምርመራ ማድረግ የማይፈልጉ ከሆነ፣ ጥገኝነት ለማግኘት ባቀረቡት ጥያቄ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል
➡️በኖርዌይ ውስጥ እንደ ልጅ ጥገኝነት ለማግኘት ማመልከት ስለሚቻልበት መንገድ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እዚህ ይጫኑ። . መረጃው በ16 የተለያዩ ቋንቋዎች ይገኛል።