እንኳን ደህና መጡ

UNHCR ኖርዌይ - ለስደተኞችና ለጥገኝነት ጠያቂዎች የሚያደርገው እርዳታ

በ UN Refugee Agency (ተመድ የስደተኞች ኤጀንሲ)፣ በ UNHCR ወደ የሚተዳደር የ‘HELP (እርዳታ)’ ድህረ-ገጽ እንኳን ደህና መጡ። እዚህ፣ ስደተኞች፣ ጥገኝነት ጠያቂዎች እና ሀገር አልባ ሰዎች፣ እንዲሁም የቤተሰባቸው አባላት እና የሚረዷቸው ሰዎች ስለ ጥገኝነት አሰራር እና በኖርዌይ ስላሉት አገልግሎቶች መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

በዚህ ድህረ-ገጽ ላይ የሚከተሉትን ያገኛሉ፦

➡️ኖርዌይ ውስጥ ጥበቃ ለሚፈልጉ ከዩክሬን ሸሽተው ለመጡ ሰዎች የሚሆን መረጃ
➡️
ከዩክሬን ብቻቸውን ለሚመጡ ሕፃናት መረጃ
➡️
ስለ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር አደጋዎች ማስጠንቀቂያዎች
➡️
ጥገኝነት ለማግኘት እንዴት ማመልከት እንደሚቻል
➡️
ለቤተሰብ ዳግም ውህደት ማመልከት
➡️
በኖርዌይ ውስጥ እርዳታ የት ማግኘት እንደሚቻል
➡️
በኖርዌይ ውስጥ ስለ UNHCR
➡️
መጥፎ ምግባርን እንዴት ሪፖርት ማድረግ እንደሚቻል

ከኖርዌይ ውጭ ነዎት? በውጭ አገር ላሉ ዘመዶች እርዳታ እየፈለጉ ነው? እባክዎን በ UNHCR እርዳታ መነሻ ገጽ ላይ መረጃ ለማግኘት ስለሚፈልጉት ሀገር ይምረጡ ወይም በአቅራቢያዎ የሚገኘውን የ UNHCR ሀገር አቀፍ ቢሮ ያነጋግሩ።

ከዩክሬን እየሸሹ ከሆነ እና በፖላንድ፣ በሃንጋሪ፣ በጣሊያን፣ በስሎቫኪያ፣ በሩማኒያ ወይም በቡልጋሪያ ውስጥ ከሆኑ እባክዎን ስለ መብቶች እና አገልግሎቶች እና የት እርዳታ ማግኘት እንደሚችሉ መረጃን በዲጂታል ሰማያዊ ነጥብ (Digital Blue Dot) ላይ ያግኙ። ጣቢያው በዩክሬንኛ እና በሩሲያኛም ይገኛል።