የእርዳታ መስመሮች

የተለያዩ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ወይም ተቋማትን በተወሰኑ ስልኮች አማካኝነት በመገናኘት ማህበራዊ የሥነ-ልቦና እርዳታን ጨምሮ ሌሎች የእርዳታና ድጋፍ ዓይነቶችን ማግኘት ይችላሉ፦

  • ራስን የማጥፋት ሐሳብ ካልዎት ወይም ራሱን የማጥፋት ሐሳብ ያለበት ሰው የሚያውቁ ከሆነ የሚከተሉትን ማነጋገር ይችላሉ፦
    • Mind Självmordslinjen (የአዕምሮ ራስን የማጥፋት መስመር) 📞 90101 (24/7 ሰዓት ክፍት ነው) በመደወል ወይም በእንግሊዝኛ እና በስዊድንኛ በሚገኘው የመስመር ላይ ውይይታቸው (24/7 ሰዓት ክፍት ነው) ይገኛል።
    • Jourhavande medmänniska (በስልክ ጥሪ ላይ የሚገኝ ሰራተኛ) በስልክ ቁጥር 📞 08-702 16 80 (በየምሽቱ ከ21፡00-06፡00) ወይም በመስመር ላይ ውይይት (ሰኞ፣ ማክሰኞ እና እሁድ ከ21፡00-24.00) በኩል በእንግሊዝኛ እና በስዊድንኛ ማግኘት ይቻላል።
  • ስለአቅራቢያዎ የአስቸኳይ ጊዜ የሥነ-ልቦና ህክምና ክፍል የህክምና ምክር እና መረጃ ለማግኘት በስዊድን ውስጥ ወደ 📞1177 (24/7 ሰዓት ክፍት ነው) ይደውሉ፣ በእንግሊዝኛ እና በስዊድንኛ ይገኛል።
  • ለሞት ፍርሃት፣ ለሀዘን፣ ለጭንቀት ወይም ራስን የማጥፋት ሀሳቦች ስሜታዊ እና መንፈሳዊ እንክብካቤ ለማግኘት በ 📞112 በመደወል Jourhavande präst (በጥሪ ላይ የሚገኝ ቄስ)ን (በየምሽቱ ከ21:00-06:00) ወይም በእንግሊዝኛ እና በስዊድንኛ በሚገኘው የመስመር ላይ ውይይት (በየቀኑ ከ20:00-24:00) ያነጋግሩ።
  • እድሜዎ ከ18 ዓመት በታች ከሆነ ወይም እርዳታ ወይም ምክር የሚፈልግ ሰው የሚያውቁ ከሆነ Bris – Barnens rätt i samhället (የልጆች መብቶች)ን በስልክ ቁጥር 📞 116 111 በመደወል (24/7ሰዓት ክፍት ነው) ወይም በእንግሊዝኛ እና በስዊድንኛ በሚገኘው የመስመር ላይ ውይይት (24/7 ሰዓት ክፍት ነው) ያነጋግሩ።

ጥያቄዎ የዚህን ‘እገዛ’ ድህረ-ገጽ ይዘት የሚመለከት ከሆነ እኛን ማነጋገር ይችላሉ።


ተዛማጅ መረጃ