ከህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር የተረፉ ከሆኑ ወይም ሌላ ሰው ከሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር የተረፉ እንደሆነ ከጠረጠሩ የስዊድን ፖሊስ በአደጋ ጊዜ ስልክ (በ 📞112 ቁጥር በመደወል) ማነጋገር ይኖርብዎታል። ከፖሊስ ጋር የሚደረግ ማንኛውም ግንኙነት በጥብቅ በምሥጢር ይስተናገዳል።
ብዙ ሰዎች በጉዞዎ ላይ እና ስዊድን ከደረሱ በኋላ ሊረዱዎት ይፈልጋሉ። ይሁን እንጂ፣ ሁሉም ሰዎች ነን የሚሉትን ላይሆኑ ይችላሉ፤ አንዳንድ ሰዎች የእርስዎን ሁኔታ ለመጠቀም ይፈልጉ ይሆናል።
ለምሳሌ፣ መጠለያ፣ መጓጓዣ ወይም ነጻ ምግብ ቃል ሊገቡልዎት ይችላሉ እና ይህን ተጠቅመው ለወሲባዊ ድርጊቶች፣ ለስራ ወይም ለሌሎች እርስዎ የማይስማሙባቸው አገልግሎቶች ጫና ሊያደርጉብዎት ይችላሉ። ወይም እርስዎን ሊጎዱ ወይም ሰነዶችዎን ወይም ሌሎች ንብረቶችዎን ሊወስዱ ይፈልጉ ይሆናል።
እባክዎን የ UNHCR ”ደህንነትን እንዴት መጠበቅ እንደሚቻል” መረጃ ሰጭ ቪዲዮን ይመልከቱ፦
ስለ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ለፖሊስ ሪፖርት ማድረግ በተመለከተ፣ ለበለጠ መረጃ እባክዎ በስዊድንኛ የሚገኘውን የስዊድን ፖሊስ ድህረ ገጽ ይጎብኙ።
እርስዎ ከዩክሬን የመጡ ስደተኛ ከሆኑ እና በስዊድን ውስጥ በሕገወጥ የሰው ልጅ ዝውውር አደጋዎች ላይ መረጃ ከፈለጉ፣ እባክዎን የስዊድን የጾታ እኩልነት ኤጀንሲን ድህረ-ገጽ ይጎብኙ፣ ይህም በዩክሬንኛ፣ በሩሲያኛ እና በእንግሊዝኛ ይገኛል።